Pages

Sunday, November 11, 2012

ኢሕአዴግ ክርስትያኖችን የሚያስፈራራበት ምናባዊ ጭራቅ፡ ‹‹ወሐቢያ››


ኢሕአዴግ ክርስትያኖችን የሚያስፈራራበት ምናባዊ ጭራቅ፡ ‹‹ወሐቢያ››

ለዛሬ ልጽፍ የፈለግኩት ስለወቅታዊው የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ሲሆን የኢሕአዴግ መንግሥት (በተለይ ደግሞ ፌዴራል ጉዳዮች) በክርስትያን ወንድምና እኅቶቻችን አዕምሮ ውስጥ ከሙስሊሞች ጋር አያይዞ እየፈጠረው ያለውን ሥጋት መሠረት አልባነት ለማሳየትም እሞክራለሁ። የሙሉውን ጽሑፌን መንፈስና ሙግት ሊጠቀልልልኝ በሚችል አንድ ዐረፍተ ነገር ብጀምር ደስ ይለኛል፡ –‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለክርስትያን ኢትዮጵያውያንም ሆነ የጋራችን ለሆነው ሕገ-መንግሥታዊ የሃይማኖት ነጻነት በፍጹም ሥጋትአይደለንም! ‹አበበ በሶ በላ ወይ?››ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹ሉሌ ካባ ለበሰ››ብሎ መመለስ ስህተት ነው! መንግሥት የተጠየቀው ቀጥተኛ የመብት ጥያቄ ሆኖ ሳለ ‹‹ኢስላማዊ መንግሥት ሊያቋቁሙ ያሰቡ አሉ››ብሎ መመለስ በምን ዓይነት አመክንዮ ነው ልክ ሊሆን የሚችለው? አወሊያ ተሰብስቦ ሰሚ ያጣ ጩኸቱን ሲያሰማ የነበረው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ መቼ ነው ኢስላማዊ -
መንግሥት እንዲቋቋምለት የጠየቀው? ‹‹ኢስላማዊ መንግሥት ይቋቋም››ያሉ ሕልመኞች ካሉስ (አሉ ወይ የሚለውን በኋላ አነሣዋለሁ) እነሱ ለብቻ ይጠየቁ እንጂ ሕዝበ ሙስሊሙ ምን አገባው? በቁም ነገር መሐል ይህን ዓይነት ቀልድ መደባለቅ እንዴት ተገቢ ሊሆን ቻለ? …ሁለት ዓላማዎችን ያዘለ መሆኑ ግልጽ ነው። አንደኛው ዓላማ መብት ጠያቂዎቹን ራሳቸውን ማስፈራራት ነው። ጥያቄያቸውን አጣምሞ በማቅረብ እና ያልተገባ ትርጉም በመስጠት እንዲደነግጡና እንዲሸማቀቁ፣ ሕዝበ ሙስሊሙና ኮሚቴዎቹ ‹‹ኧረ እኒህ ሰዎች አመረሩብን!››በሚል ፍርሐት ተወጥረው ጥያቄያቸውን እንዲተዉት ነው። ሁለተኛው ዓላማ ደግሞ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን (በዋነኝነት ሕዝበ ክርስትያኑ) የሸሪዓ መንግሥት የማቋቋም ዓላማ (ሕልም ብለው ይቀላል) ያለን መስሏቸው እንዲደነግጡና ከጎናቸው እንዲቆሙ ለማድረግ ነው። እየተነዛ ያለውን ፕሮፓጋንዳ ሐሰትነት ማሳየት ደግሞ ከባድ አይደለም። እውነታዎቹን በዚህ ጽሑፍ አብረን እናያቸዋለንና። እስቲ ከመሠረቱ ለመጀመር ይህ ኢስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም በመንቀሳቀስ እየታማ ያለው ምናባዊ ጭራቅ “scapegoat”(ወሐቢያ) ምን እንደሆነ ለማየት እንሞክር።
‹‹ወሐቢያ››ምንድነው?
‹‹ወሐቢያ››ባሁኑ ሰዓት እጅግ ተለጥጦ የመጅሊስ ተቃዋሚዎች የወል ሥም ሊሆን ምንም ያህል አልቀረውም። እኛ ግን መጀመሪያ ትክክለኛ ትርጉሙን እንየው።
‹‹ወሐቢያ››ሥሙ ራሱ የተወሰደው ‹‹ሙሐመድ ኢብን ዐብዱልወሐብ››ከተባሉ የኢስላም ምሁር ሲሆን ሸኹ ከሁለት መቶ  ዓመታት በፊት ዐረቢያ ውስጥ ኢስላማዊ አምልኮዎችን ከባሕል ተጽእኖ ለማላቀቅ የታገሉ መሆናቸው ይነገርላቸዋል። ይከተሉት የነበረው የአስተሳሰብ መስመር ዋነኛ አነቃቂ የነበሩ በመሆናቸው ሥማቸው የበለጠ ገኖ ሊወጣ ችሏል። በሂደት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ የእኒህን ሸኽ ሃይማኖታዊ የአስተሳሰብ መስመር የሚከተሉ ሙስሊሞች ‹‹ወሐቢያ››በሚል መጠራት ጀመሩ። ይህ ሥያሜ ደግሞ በነገራችን ላይ ተለምዷዊ እንጂ መደበኛ ሥም አይደለም። እነሱም ራሳቸውን የሚጠሩት ሙስሊሞች እንጂ ‹‹ወሐቢያ››በሚል አይደለም። ልክ መንፈስን በማጥራት ላይ ያተኩር የነበረው አስተሳሰብ ተከታዮች ‹‹ሱፊያ››ተብለው ይጠሩ እንደነበረው ሁሉ ‹‹ወሐቢያ›ም በተለምዶ የሚታወቀው በአምልኳዊ የአስተሳሰብ መስመርነቱ እንጂ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴነቱ አይደለም። ተጽእኖውም በሙስሊሙ ኅብረተሰብ አምልኳዊ አፈጻጸም ላይ የተወሰነ ሆኖ ነው የምናገኘው። ይኸው የአስተሳሰብ መስመር ታዲያ የሚታወቅባቸው አመለካከቶች (ፈትዋዎች) ነበሩት፤ አሉትም። ለምሳሌ ነቢዩ ሙሐመድ የተወለዱበትን ቀን እንደበዓል አድርጎ ማክበር ትክክል እንዳልሆነ ያምናሉ፤ ያስተምራሉ። ጺም ማሳደግና ሱሪን ማሳጠር ተገቢ እንደሆነም  ያስተምራሉ። ሌሎችም አመለካከቶች አሏቸው።ባጭሩ ምንም እንኳ ሥያሜውን የሚቀበሉም ሆነ ራሳቸውን ‹‹ወሐቢያ››በሚል የሚገልጹ ሙስሊሞች ባይኖሩም በተለምዶ ‹‹ወሐቢያ››ተብለው የሚጠሩት ከላይ የጠቀስናቸውን ኢስላምንና ሙስሊሞችን ብቻና ብቻ የተመለከቱ አመለካከቶችን የሚያቀነቅኑ ሙስሊሞችን ነበር። ዛሬ ግን አዘውትረው በእምነታችን ጣልቃ እየገቡ ለያዥ ለገራዥ ያስቸገሩን የተከበሩ ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው መጥተው ‹‹አይ! ወሐቢያ ማለት ኢስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም እንቅስቃሴ የሚያደርግ ቡድን ነው!››እያሉን ይገኛሉ። እንዴት ነው ነገሩ…እርስዎ ከኛ በላይ ስለሃይማኖታችን ያውቁ ይሆን እንዴ የተከበሩ ሚኒስትር?
እስቲ የተወሰኑ ጥያቄዎችን አንሥቼ ራሴ እየመለስኳቸው ልሂድ…ለመሆኑ ‹‹ወሐቢያ››የሚባል በመደበኛ መልኩ የተዋቀረ ድርጅት በአገራችን አለ እንዴ?
እኔው ልመልሰው። ‹‹ወሐቢያ››የሚባል ተቋም ከነጭራሹ በአገራችን የለም። ‹‹ወሐቢያ››ኢስላማዊ የአስተሳሰብ መስመር እንጂ ቡድን አይደለም። አስተሳሰቡም ኢስላም ላይ ብቻና ብቻ የተወሰነ ነው –መንግሥትን የሚመለከት አይደለም። አንድ ሙስሊም ደግሞ የፈለገውን የአስተሳሰብ መስመር መርጦ መከተል ይችላል –በዚህ መንግሥት ሊረበሽ አይገባውም። ጋዜጠኛ ሑሴን ኸድር ሰሞኑን በዕንቁ መጽሔት ‹‹ነፋስን በወጥመድ››በሚል ርእስ ያወጣው ጽሑፍ ወሐቢያ የሚባል ተቋምም ሆነ ቡድን አለመኖሩን በመጥቀስ መንግሥት በ‹‹ወሐቢያ››ላይ የጀመረው ዘመቻ ንፋስን በወጥመድ ለመያዝ ከመሞከር ያልቀለለ መሆኑን አሳይቶ ነበር። በምክንያነት የጠቀሰውም ‹‹ወሐቢያ››አስተሳሰብ እንጂ ቡድን አለመሆኑን ነበር።
ሌላ ሊረሳ የማይገባው ነገር ደግሞ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ከዓለማቀፉ ኢስላማዊ እንቅስቃሴም ሆነ የግጭት ክስተቶች የሚለይበት በርካታ ነጥብ እንዳለ ነው። ይህን አስመልክቶ ሰፊ ጥናት ያደረጉ የውጭ ምሁራኖች በሽ ናቸው። እዚሁ ቅርብ ሆኖ፣ በሩቁ ሳይሆን አብሮ ከሙስሊሙ ጋር ኖሮ ለዓመታት በርካታ ጥናቶችን ያጠናው ኖርዌያዊው ዶክተር ቴሪ አስቴቦ ከመሰል ምሁራን አንዱ ነው፡ ፡ የእሱን ጥናት ወረቀቶች እና ድምዳሜዎች ማየቱ ብቻውን በሥም መመሳሰል ከመሸወድና በሌላው ዓለም ያሉ ክስተቶችን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ በሐሰት ከመደፍደፍ ያድናል፡፡
ሃይማኖታዊ ግጭቶችን ከእንቅስቃሴ ጋርየማደባለቅ አባዜ
የሕዝበ ሙስሊሙን የልብ ትርታ ከማዳመጥ እጅግ የራቁ አንዳንድ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ይህንኑ ‹‹ኢስላማዊ መንግሥት ሊያቋቁም የሚፈልግ ቡድን አለ››የሚል ባዶ ክርክራቸውን ለሌሎች ለማሳመን ከሚያቀርቡት መረጃ አንዱ ካሁን ቀደም የተከሰቱ የሃይማኖት ግጭቶችን ደጋግሞ ማንሣት ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስትያኖች በሕዝብ ደረጃ በጥሩ መቻቻል ታሪካችንን አሳልፈናል። ሃይማኖታዊ ጭቆና ሲያደርሱ የነበሩትም መሪዎች እንጂ ሕዝቡ እርስ በርስ በመተሳሰብ ነው ለዘመናት የኖረው። ይሁንና ይህ ማለት ግን የሃይማኖት ግጭቶች እዚህና እዚያ አልተከሰቱም ማለት አይደለም። በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ እጅግ ጥቂት ጽንፈኞች መኖራቸውና ግጭት ፈጥረው ማወቃቸው ግልጽ ነው። በዚህ ሁላችንም ብናዝንም እኒህ ግጭቶች ግን የአብሮነት ሕይወታችንን ያደበዘዙ አልነበሩም። የዘመነኛው የአብሮነት ታሪካችን ዋነኛ አካልም አይደሉም። ይልቁንም በኩንታል ስንዴ መሐል የተገኙ ጥቂት እንክርዳዶች ናቸው፤ አልያም በኩንታል ጤፍ መሐል የተሰነቀሩ ጥቂት ጉድፎች!
በነዚህ ግጭቶች ያላዘነ ማንም የለም። ጅማ ውስጥ የነበሩት ግጭቶች የሁላችንንም ልብ አድምተዋል። እኔ በግሌ ሙስሊም ብሆንም አንድ ቤተ ክርስትያን ሲቃጠል በጣም እበሳጫለሁ፤ ጓደኞቼም ቢሆኑ ያዝናሉ። ማንም ጥቂት እንኳ የአማኝ መልካምነት በልቡ ያለው ክርስትያንም ሆነ ሙስሊም በዚህ መሰል ድርጊቶች ማዘኑ አያጠራጥርም። እኔ ለምሳሌ በርካታ ክርስትያን ጓደኞች አሉኝ። ሁሉም ግን ሙስሊም ባይሆኑም ጉራጌ ዞን ውስጥ በተቃጠሉት መስጊዶች አዝነዋል፤ ቅዱስ ቁርኣን በአንዳንድ አካባቢዎች ለመጸዳጃነት በመዋሉም ተከፍተዋል። ልክ እንደክርስትያን ወንድሞቹ እና እኅቶቹ ሁሉ ሕዝበ ሙስሊሙም ክርስትያኖች ላይ በአንዳንድ ጽንፈኞች የተፈጸሙ አስከፊ ድርጊቶች ይረብሹታል፤ ያሳዝኑታል። እስካሁን በጽንፈኞች በተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናትም በጣም አዝኗል።
ጥንታዊው ዋልድባ ገዳምን በተመለከተም ሆነ የዝቋላ ደን ቃጠሎ ለቤተ ክርስትያኑ ደህንነት አስጊ መሆኑ የክርስትያኖች ብቻ ሳይሆን የኛም ችግርና ሥጋት ነው። በአሕባሽ ምክንያት እየተፈጠረብን ያለው ዘርፈ ብዙ አገራዊ ችግርም ቢሆን ለሕዝበ ክርስትያኑም ጭምር አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን ከተወያየኋቸው ክርስትያን ሰባኪያንም ሆነ ከጓደኞቼ ብዙ ሰምቻለሁ። ይህ ከሞላ ጎደል የአብሮነታችን እውነታ፣ ማንም ጨካኝ ንጉሥ እንኳ ከልባችን ሊፍቀው ያልቻለው የእርስ በርስ መተዛዘናችን ውጤት እንደሆነ ይሰማኛል።
ለነዚህ ጥቂት ግጭቶች በተለየ ተጠያቂ የማደርገው ሃይማኖት አይኖርም፤ በሁላችንም መሐል እጅግ ጥቂት ጽንፈኞች መኖራቸውን እረዳለሁና። የኔ ሙግት ‹‹እነዚህ ጥቂት ግጭቶች ጽንፈኞች በሚያደርጓቸው የሃይማኖት ትንኮሳዎች ምክንያትነት የሚፈጠሩ ናቸው እንጂ የእንቅስቃሴ ውጤቶች አይደሉም››የሚል ነው። ለምሳሌ አንድ ቦታ ላይ አንድ ጽንፈኛ ሰው በሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ የሆነ ግላዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ ቢሰነዝር፣ እነሱ ደግሞ ተናድደው የሆነ ሌላ ጽንፈኛ እርምጃ ቢወስዱ ‹‹ግጭት ተፈጠረ››እንላለን እንጂ ግጭቱን እንቅስቃሴ ወለድ አናደርገውም።
በነገራችን ላይ በሃይማኖት ግጭት ውስጥ የተሳተፈ ሁሉ ‹‹ጽንፈኛ ነው››የሚል ድምዳሜ እየሰጠሁ አይደለም። ግጭት ‹‹ሃይማኖቴ ተነክቷል››ብሎ ባሰበ፣ ተነክቶበት በተቆጣም ሆነ በተሳሳተ መረጃ (false alarm) ምክንያት በንጹሐን ሰዎች ሊፈጸም ይችላል። ስለዚህ በጥቅል ሁሉንም በ‹‹ጽንፈኝነት››ቅርጫት ውስጥ እየከተትኩ አይደለም።
ከላይ የጠቀስኳቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ግን እኒህን ግጭቶች በማውሳት ‹‹ኢስላማዊ መንግሥት የማቋቋም ዓላማ ያላቸው ሰዎች አሉ››የሚለውን ንግግራቸውን ሊግቱን ይሞክራሉ። ይህ ከባድ ስህተት ነው። ሃይማኖታዊ ግጭት ሌላ…ኢስላማዊ መንግሥት መመሥረት ሌላ! ምን አገናኛቸው? ለምንስ ነው አላስፈላጊና ባዶ ሥጋቶችን በሕዝቡ ላይ በመጫን እርስ በርስ በዐይነ ቁራኛ የሚተያይ ትውልድ ለመፍጠር የሚጥሩት? የሕዝብ በዘርና በሃይማኖት የጎሪጥ መተያየት ለማንም አይጠቅምምኮ!
በጣም የሚገርመው ነገር ፌዴራል ጉዳዮች በተደጋጋሚ ለጋዜጠኞች እና ለሕዝብ ግንኙነት ሠራተኞች በሰጠውና እኔም ራሴ በተገኘሁበት ሥልጠና ‹‹የሃይማኖት ግጭቶችን ስትዘግቡ ግጭቱን በማያባብስ መልኩ መሆን አለበት። ማጋነን እና መደጋገም አያስፈልግም››እያሉ ደጋግመው አስተምረውን ነበር። የተከበሩ ዶክተር ሽፈራው ራሳቸው ይህንኑ አጽንኦት ሰጥተው ደጋግመው ነግረውናል። ዛሬ ግን ራሳቸው በተመሣሣይ ስህተት ላይ ሲወድቁ እያየናቸው ይመስላል። ሕዝበ ሙስሊሙ ያነሣውን የመብት ጥያቄ ለማድበስበስ በሚመስል አኳኋን ‹‹ወሐቢያ የሚባል ቡድን እስላማዊ መንግሥት ሊመሠርት ተነስቷል!››እያሉ ክርስትያን ወንድሞቻችንን እያስበረገጉ ነው።
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ለብቻ በሌላ ጉዳይ
ላይ ቢሆን ቢያንስ ‹‹ስለማናውቃቸው ሌሎች ቡድኖች እያወሩ ነው››እንል ነበር። እሳቸው ግን ይህንኑ እያሉ ያሉት ስለሕዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ሲጠየቁ በመሆኑ ‹‹ወሐቢያ››በሚል የምናባዊ ጭራቅ ሥያሜ ጥቃት እየሰነዘሩ ያሉት ሙስሊሙ ላይ ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ተገቢ አይደለም።
እኛ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሸሪዓ መንግሥት እንደማንፈልግ ሦስት ተጨባጭ ምክንያቶችን እንደሚከተለው እጠቅሳለሁ፡-
1. ዓለማዊው ሕገ-መንግሥታችን በቂያችን ነው!
 በ 1987 የጸደቀው ሕገ-መንግሥት በውስጡ ያዘላቸው ሃይማኖትን የተመለከቱ አንቀጾች የሕዝበ ሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ፍላጎት ለማሟላት እጅግ በቂ ናቸው! በዋነኝነት የሃይማኖትና መንግሥት መለያየት፣ የአንዱ ባንዱ ጣልቃ አለመግባት እና የመንግሥታዊ ሃይማኖት አለመኖር እጅግ መሠረታዊና በሙሉ ልብ የምንቀበላቸው ወርቃማ አናቅጽት ናቸው። በተጨማሪም አንድ ሰው የፈለገውን ሃይማኖት ያለማንም አስገዳጅነት መምረጥ፣ መስበክ፣ ማስፋፋት፣ እንዲሁም ከመሰሎቹ ጋር ተባብሮ ተቋም የመመሥረት መብት እንዳለው ይኸው ሕገ-መንግሥታችን አስቀምጦታል። እኒህን ሕገ-መንግሥታዊ መብቶችና ነጻነቶች ልክ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሙሉ ልባችን እንቀበላቸዋለን። የትኛውም ሙስሊም ቢጠየቅ ከዚህ ውጭ ፍላጎትም ዓላማም የለውም። የሌሎችን የማመን መብት ለመጋፋትም የሚፈልግበት ምክንያታዊ መነሻ የለውም።
ሕዝበ ሙስሊሙም ቢሆን ያነሣው ጥያቄ ‹‹አሕባሽ የተባለው ቡድን መጥቶ ይህን ሕገ-መንግሥታዊ መብታችንን እየነፈገን ነው! አንድ በሉልን! በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አትግቡብን! የተቋም መሪዎቻችንን እራሳችን እንድንመርጥ ዕድል ስጡን!››የሚል እንጂ የኢስላማዊ መንግሥት ጥያቄ አይደለም። ይህ ሙስሊሙም ክርስትያኑም፣ ቡድሂስቱም ሂንዱዪስቱም አንድ ላይ በሚኖርባቸው አገራት ሁሉ በተጨባጭ የሚታይ እውነታ ነው። በሙስሊሙ ዓለም እንደ ተምሳሌት የሚቆጠሩ አንድ እውቅ ዶክተር ይህንኑ አስመልክተው ሕንድ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ሲናገሩ የሚከተለውን ተናግረው ነበር፡ –‹‹በእስልምና ግዴታ የተደረገብኝን ነገር ከመፈጸም የሚከለክለኝም ሆነ በእስልምና ክልክል የሆነን ተግባር እንድፈጽም የሚያስገድደኝ ዓለማዊ ሕግ እስካሁን ሕንድ ውስጥ የለም። ስለዚህ በሕንዳዊነቴ እኮራለሁ!››ነበር ያሉት።
2. ሸሪዓ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማቋቋም ማሰብ አዋጭአይደለም!
እንደው ከተራ ሥሌት አንጻር እንኳ ብናስበው ሸሪዓን ኢትዮጵያ ውስጥ ማቋቋም በፍጹም አዋጭ አይደለም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊ እና ሕብረ ሃይማኖታዊ አገር ናት። የተለያዩ እምነት ተከታዮች በከፍተኛ ቁጥር በሚገኝበት አገር ውስጥ ሸሪዓ እንዴት አዋጭ ሆኖ ሊታሰብ ይችላል? እዚህች አገራችን ውስጥኮ ቢያንስ 40 ሚሊዮን ክርስትያኖች አሉ። ይህን ያህል ቁጥር ያለው ክርስትያን ባለበት አገር ውስጥ ሸሪዓ የማቋቋም አጀንዳ ይዞ አንድ ቡድን እንዴት ሊነሣ ይችላል? ሥሌቱ በፍጹም ልክ አይመጣም!
የአገሪቱ ግማሽ ሕዝብ የማያምንበት የእምነት መጽሐፍ በየትኛው ኃይል ነው መተዳደሪያ ሊሆን የሚችለው? እንዲህ ዓይነት የማይሳካ ሕልም ሰንቆ የሚንቀሳቀስ ኢስላማዊ ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ በፍጹም የለም! ሊኖርም አይችልም። ቢኖርም ከማንም በፊት ፊት የሚነሣው ሕዝበ ሙስሊሙ ራሱ ነው። ከእልቂት ያለፈ በተጨባጭ ሊፈጥረው የሚችለው ውጤትም የለም!
ሙሉ በሙሉ ሙስሊም ባለባቸው አገራት ውስጥ ሸሪዓ ማቋቋም የራሱ ትርጉምም ሆነ አስፈላጊነት ሊኖረው ይችላል። ያ የአገሪቱ ሕዝብ በራሱ ምርጫ የሚወስነው ጉዳይ ነው። ሌላው ቀርቶ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም ሆነው እንኳን ሸሪዓ ያልተቋቋመባቸው ምን ያህል አገራት እንዳሉ ብናስበው ቁጥሩ የትዬለሌ ነው። ከነጭራሹ የሸሪዓ አስተዳደር ያለባቸው አገራት ቁጥር ከአንድ እጅ ጣት አይበልጥም። ታዲያ ከዚህ በላይ ያልተጨበጠ ሥጋት ከየት መጥቶ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ሸሪዓን ለማቋቋም የሚንቀሳቀስ ቡድን አለ በሚል በገደምዳሜ ወደ ሕዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ጣት የሚቀሰረው? ሕዝበ ሙስሊሙን በጅምላ እና ተከሳሹን አካል ለይቶ ባላወጣ መልኩ መፈረጅ ክርስትያኖችን በውሸት ሥጋት ለማስደንገጥ ካልሆነስ እንዴት ሊጠቅም ይችላል?
3. ጥያቄዎቻችን ከመሠረታዊነት ዘለው አያውቁም!
እኛ ሙስሊሞች እንደ ሕዝብ ስናነሣቸው የነበሩት የመብት ጥያቄዎች ከመሠረታዊነት ዘለው አያውቁም። በኢሕአዴግም ዘመን ቢሆን በተለይ ላለፉት አምስት ዓመታት ስንጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች ከሕግ አንጻር እጅግ ትናንሽ ነበሩ፤ ናቸውም። ‹‹ሴቶቻችን በትምህርት ቤት ሂጃብ አይከልከሉ፤ ወንዶቻችን ትምህርት ቤት ውስጥ ሶላት መስገድ አይከልከሉብን፤ እምነታችን የማንነታችን አካል ነውና እንደጃኬት አውልቀነው ልንገባ አንችልም፤ ሕገ-መንግሥቱ የደነገገውን መብት የትምህርት ተቋማት ዲኖችና ዳይሬክተሮች አይከልክሉን!››ከማለት ያለፈ ጥያቄ አላነሣንም። ‹‹አሜሪካን በመሳሰሉ የሴኪውላሪዝም ተምሳሌት አገራት እንኳ የሚፈቀዱ ተግባራትን አንከልከል››ከማለት ውጭ ምንም አላልንም። ነው ወይስ የኢትዮጵያው ሴኪውላሪዝም ከአሜሪካው እንኳ ተሸሎ ተገኘ?
ተቋማችንን መጅሊስም ቢሆን ‹‹በመረጥናቸው ሰዎች ይተዳደር››ከማለት የዘለለ ምንም አላልንም። ይህ ደግሞ ‹‹በዴሞክራሲ አስተዳድራለሁ››ለሚል መንግሥት እጅግ ቀላልና ቀጥተኛ ጥያቄ ነው፤ ውስብስብ አይደለም። እንኳንስ የእምነት ተቋምና መንግሥትም ቢሆን በሕዝቡ መመረጥ አለበት ተብሎ አይደል ምርጫ የሚባል ነገር ያስፈለገው?
 ከአመክንዮአዊ አስተሳሰብ እናፈንግጥ ካላልን በስተቀር እኒህን የመሳሰሉ መሠረታዊ መብቶቹ እንዲጠበቁለት የሚታገል ሰው ሸሪዓ ለማቋቋም ሊያስብ አይችልም! በጭራሽ! አንድ ጠኔ ያጠማረረውና በረሐብ ሊሞት የደረሰ ሰው ‹‹ምግብ ስጡኝ››ብሎ ሊጠይቅ ይችል ይሆናል እንጂ ‹‹ዶሮ ወጥ ካልሰጣችሁኝ አንቄ እገላችኋለሁ!››ብሎ ሊያስፈራራ ይችላል ብሎ ማሰብ ከምክንያታዊነት ጋር እጅጉን ይጣረሳል። በተመሳሳይ ሁኔታ አንዲት ‹‹ሻሼን ሳላወልቅ እንድማር ፍቀዱልኝ!››እያለች የምትማጠን ምስኪን እኅታችንን ‹‹ሸሪዓን ለማቋቋም እያሰበች ነው››ብሎ መክሰስ፣ አንድ ‹‹ከሊባኖስ ያመጣችሁትን ሃይማኖት አልፈልግምና ባካችሁ ሰላም ስጡኝ!››እያለ የሚማጠን ምስኪን ወንድማችንን ‹‹ሸሪዓን ለማቋቋም ዶልተሃል››በሚል መወንጀል ከእውነታው ሃዲድ የሚያስፈነግጥ አቋም ነው። ይህንን የምለው ባለሥልጣናቱ ስለሸሪዓ የማቋቋም እንቅስቃሴ ሲያወሩ እየጠቆሙ ያሉት ወደእነዚህ የመብት ጥያቄዎች ስለሆነ ነው! በእውነቱ በጣም ተሳስተዋል! ኢስላማዊ መንግሥት ይቅርና ትዳር ነክ ጉዳዮቻችንን ለፈለገ ሰው ለማስተናበር የተቋቋመው ሸሪዓ ፍርድ ቤታችን እንኳ በፈርጀ ብዙ ችግሮች የተጠፈረ ተቋም ነው። እሱን እንኳ ለማስተካከል አቅም የሌላቸው ሰዎች ‹‹ሸሪዓ ሊያቋቋሙ ያስባሉ››ብሎ መጠርጠር እንኳ የማይታለምና የማያስኬድ ነው።
መንግሥትን በካራቴ?!
ፌዴራል ጉዳዮች በቅርቡ ባዘጋጀው የጋዜጠኞች ሥልጠና ላይ ሕዝበ ሙስሊሙን በጭራሽ ያላገናዘበ ለብ ለብ ወረቀት ያቀረቡ አንዲት ወይዘሮ ‹‹ሙስሊም ካራቴ አሠልጣኞች በዝተዋል››የሚል አስገራሚ እውነታ ከጠቀሱ በኋላ ይህንኑም ከዚሁ ‹‹ኢስላማዊ መንግሥት የማቋቋም አባዜ››ጋር አያይዘውታል። ‹‹የባሰው መጣ››ይሏል ይሄ ነው! እንዴት ዓይነት ጉደኛ ድምዳሜ ነው ይሄ? ‹‹ሙስሊም ካራቴ አሠልጣኞች በዝተዋል አልበዙም››የሚለውን ማረጋገጡ ሌላ ጥናት የሚፈልግ ነገር ሆኖ ‹‹እንዲህ ዓይነት ድምዳሜ እንዴት ሊወስዱ ቻሉ?››ብለን ብንጠይቅ መልሱ ‹‹ክርስትያኖችን ከማስፈራራት ውጭ ሊሆን አይችልም››ነው።
አንድ ቀላል ጥያቄ ለወይዘሮዋ ብንጠይቃቸው ሥጋታቸው ባዶ መሆኑን እንረዳለን…ለመሆኑ መንግሥት የሚቋቋመው በካራቴና በጫማ ጥፊ ነው እንዴ? ኢሕአዴግ ጦረኛውን ደርግ ደምስሶ የገባው ካራቴ ስለሠለጠነ ነበር እንዴ? ለምን የማይመስል ማስፈራሪያ እየፈጠራችሁ ክርስትያን ወንድሞቻችንን ታስበረግጋላችሁ? ለምን በአሉባልታ ታቃቅሩናላችሁ? ለምንስ ትከፋፍሉናላችሁ?
አንድ መንግሥት ለመገልበጥና የራሱን መንግሥት ለማቋቋም የሚፈልግ ቡድንኮ ከተማ ውስጥ ካራቴ ከመሠልጠን ይልቅ ጫካ ነው የሚገባው! በሊማሊሞ ነው የሚያቋርጠው! ታዲያ የትኛው ጫካ ውስጥ ታጥቀን ገብተን ነው እንዲህ ዓይነት ሐሜት የሚነዛብን?
የትኛውም ሃይማኖት ቢሆን ስገምት ለስፖርታዊ እንቅስቃሴና ለአካል ብቃት ጥሩ ዕይታ ይኖረዋል። እስልምናም ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም። ሙስሊም ካራቴ አሠልጣኞች በዝተውም ከሆነ ለምን ከኢስላማዊ መንግሥት የማቋቋም ተረት ጋር እንዳያያዛችሁት ለኔ ግራ ነው። በአንድ ሙያ ላይ የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች በዛ ብለው ከታዩ ሌላ ነገር ለመጠርጠር የምንፈጥን ከሆነማ በጣም ችግር ይፈጠራል። ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ነገሮችን አንባቢያን ራሱ ቢያስቧቸው አመክንዮው ምን ያህል ፉርሽ እንደሆነ መረዳት ይችላሉ። አንድ ጥሩ የካራቴ ተማሪ በዛ ቢባል ያናደደውን ሰው በቦክስ ሊዘርር ይችል ይሆናል እንጂ መንግሥት አይገለብጥበትም። ደግሞም መንግሥት በሥርዓቱ እውቅና ሰጥቶ ግብር የሚሰበስብባቸውን የካራቴ ትምህርት ቤቶች በዚህ ዓይነት አሉባልታ ሥማቸውን ማጥፋት ተገቢ አይደለም። ሰዎቹ እንደተባለው ‹‹መንግሥት ለመገልበጥ››ከሆነ እየተማሩ ያሉት ፈቃድ የሰጣቸው አካል ራሱ በሕግ ተጠያቂ ከመሆን አያመልጥም።
አዎን! አስተማሪያችን ነቢዩ ሙሐመድ
‹‹ጎረቤቱ ተንኮሉን የማያምነው ሰው በእርግጥም አላመነም››ብለውናልና ለጎረቤቶቻችን እንኳ የሥጋት ምንጭ መሆን አንፈልግም። አገራችን ለሁላችንም በቂ ናት! የሚያሻንም የጋራ ሕልም እንጂ ዘወትር በመካከላችን ተቀብሮ ሰላም የሚነሣ የጥላቻ ሰንኮፍ አይደለም! ክፍፍል ይብቃን።
አላህ ኢትዮጵያን ይባርክ!

ኑ ከኛ ተማሩ

ኑ ከኛ ተማሩ! ስቃዬ ቢበዛ ቢያይል ክፉኛ : ግፉ ቢበረታም ቢሆን አደገኛ : ጠጠር አናነሣም አንረብሽም እኛ : የኢስላም ልጆች ነን የሠላም ዘበኛ : ለይስሙላ ብቻ ተው ብዙ አታውሩ : ሠላምን በተግባር ኑ ከኛ ተማሩ!!!

ከአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ


ከአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ

‹‹በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሃይማኖት ነጻነት መብት ጥሰት ያሳስበናል››

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ከቀን ወደቀን እየጨመረ የመጣው የሃይማኖት ነጻነት መብት ጥሰት ድርጅታችንን (የአሜሪካ መንግስት አለም
አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን) በጣም ከሚያሳስቡት ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ከጁላይ 2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አስቀድሞ የነበረውን የሃይማኖት አንጃ ለመቀየር የጣረ ሲሆን ሂደቱን የተቃወሙ የሃይማኖት አባቶችን እና ሰባኪዎችንም እየቀጣ ይገኛል፡፡ በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተሳተፉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሲታሰሩ ቆይተዋል፡፡ በ 29 ኦክቶበር 2012 መንግስት ዘጠኝ ያህል ተቃዋሚዎችን በሽብርተኝነት እና ኢስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ሙከራ በማድረግ ወንጀል ከሷቸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ አንድን የሃይማኖት አንጃ በግድ በመጫን ሃይማኖታዊ አተገባበሮችን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት ያስነሳበትን ተቃውሞ ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግስት ካደረጋቸው ሙከራዎች ውስጥ ይህኛው በጣም አሳሳቢው ነው›› ይላሉ የአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ኮሚሽነር አዚዛ አል ሂብሪ፡፡ ‹‹የተከሰሱት ግለሰቦች ህገ-መንግስታዊ እና በአለምአቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን የሃይማኖት ነጻነት መርሆዎች መጣስ በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ከነበሩ አስር ሺዎች መካከል አባል የሆኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን አቁሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና በአስቸኳይ ያላግባብ የተከሰሱትን ግለሰቦች ሊፈታ ይገባል›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በአብዛኛው የሱፊ መስመር ተከታይ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ካለፈው ጁላይ 2011 ጀምሮ አል አህባሽ የተባለውን የሃይማኖት አንጃ በግድ ለመጫን ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫንም ራሱ በሚፈልገው መልኩ አካሂዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር የዋለ እንደሆነ ተደርጎም ይታሰባል፡፡ በመንግስት እየተፈጸመ ያለው እስራት፣ የሽብርተኝነት ክስ እና የመጅሊስ ምርጫ ቁጥጥር ማስረጃ ሆኖ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ነጻነት አደጋ ውስጥ መግባቱንና መንግስትም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የመቆጣጠር ፍላጎቱ እያደገ መምጣቱን ነው፡፡
‹‹የአሜሪካ መንግስት ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ የሚሰጠውን የአገሪቱን ህገ መንግስት እና አለምአቀፍ ድንጋጌዎች ማክበር እንዳለበት ለአዲሱ የኢትዮጵያ አስተዳደር ማስገንዘብ ይኖርበታል፡፡ የአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን አክራሪነትን በመዋጋት ስም ሃይማኖታዊ ጭቆና ማድረስ የበለጠ ወደአክራሪነት የሚገፋ፣ አለመረጋጋትን የሚፈጥር እና ወደብጥብጥም የሚመራ መሆኑን ይረዳል›› የሚሉት ደግሞ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ካትሪና ላንቶስ ስዌት ናቸው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ካላት ጂኦ ፖለቲካዊ አስፈላጊነት እና ሙስሊሞችም ከአገሪቱ ጠቅላላ ህዝብ አንድ ሶስተኛ ያህል እንደመሆናቸው መንግስት የሃይማኖት መብት ጥሰቱን አቁሞ ሃይማኖታቸውን በሚፈልጉት መልኩ እንዲተገብሩ ሊፈቅድላቸው ይገባል፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ለአደጋ ተጋላጭ የሆነው ይኸው ክልል ወደበለጠ አለመረጋጋት የሚሸጋገርበት እድል ሰፊ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የጉዳዩ የኋላ ታሪክ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው የሚተገበረው የሱፊ እስልምና መስመር መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 27 ደግሞ ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ የሚሰጥ ሲሆን መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንዳይገባ ይደነግጋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን አገሪቱ ውስጥ ‹‹ወሀቢዝም›› እየተስፋፋ መጥቷል በሚል እሳቤ ከሊባኖስ የሃይማኖት ምሁራንና ኢማሞችን በማምጣት ለተማሪዎቻችው እና ተከታዮቻቸው ያስተምሩ ዘንድ ለኢትዮጵያውያን ኢማሞች እና መምህራን ስልጠና እንዲሰጡ አድርጓል፡፡ ስልጠናውን ለመውሰድና ለማስተማር ያልፈቀዱ ኢማሞችን ከስራቸው ያባረረ ሲሆን መስጊዶችንና ትምህርት ቤቶችንም ዘግቷል፡፡ ይህንን በመቃወም ነው እንግዲህ በየአርብ ስግደቶቹ ላይ በተለያዩ መስጊዶች ሰላማዊ ተቃውሞ ሲደረግ የቆየው፡፡ ተቃውሞዎቹ በአገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄዱ የቆዩ ቢሆንም ማእከል ያደረጉት ግን የአዲስ አበባውን አወሊያ ትምህርት ቤት እና መስጊድ ነበር፡፡

ተቃውሞዎቹ ሲቀጥሉ ባለፈው ጸደይ ህዝቡ 17 ታዋቂ ግለሰቦችን በአስታራቂነት (በመፍትሄ አፈላላጊነት) በመምረጥ ከመንግስት ጋር ድርድር እንዲያደርጉ ልኳል፡፡ ድርድሩም በሚከተሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ነበር፡- 
1. መንግስት ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ የሚሰጠውን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ እንዲያከብር
2. መንግስት አል አህባሽ የተባለውን አንጃ በሙስሊሙ ላይ በግድ መጫኑን እንዲያቆምና አህባሽ እንደማንኛውም ሃይማኖት በራሱ ብቻ እንዲንቀሳቀስ
3. የተዘጉ መስጊዶችና ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ዱሮ ለነበሩት ኢማሞችና አመራሮች እንዲመለሱ
4. ለመጅሊስ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድና የሚካሄድበት ቦታም የመራጩን ህዝብ ውሳኔ ለማክበር ሲባል በቀበሌዎች እንዲሆን 

ሆኖም ድርድሩ ሳይሳካ በመቅረቱ ተቃውሞዎቹ በመጠንና በተደጋጋሚነት ጨምረው ነበር፡፡ በምላሹ የኢትዮጵያ መንግስት የታጠቁ ሃይሎችን አሰማርቶ ከበባ በማድረግ እና ቤት ለቤት ፍተሻዎችን በማካሄድ ሰላማዊ ሙስሊሞችን ለማስፈራራት ሲሞክር ቆይቷል፡፡ መንግስት ከጁላይ 13 እስከ 21 የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና በትንሹ ሰባ ያህል ተቃዋሚዎችን ማሰሩን የገለጸ ቢሆንም ተቃዋሚዎች ግን የታሰሩት ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠር መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ሂደትም ሆነ በእስር ቆይታቸው ወቅት ፖሊስ ትርፍ ሃይል መጠቀሙንም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩት ብዙዎቹ በአሁኑ ወቅት ተለቀዋል፡፡ ዘጠኝ የኮሚቴው አባላት ግን አሁንም በእስር ላይ ነው የሚገኙት፡፡ 

በኦክቶበር 29 መንግስት በተቃዋሚዎቹ እና በዘጠኝ የኮሚቴው አባላት ላይ ያቀረበው ክስ የመጀመሪያው ሲሆን ግለሰቦቹ ሲታሰሩ የተወሰዱትም የፖለቲካ እስረኞች ወደሚታሰሩበት እና ተደጋጋሚ ቶርቸር ወደሚፈጸምበት የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ማእከላዊ ነው፡፡ የተከሰሱትም ሽብርተኝነትን ከመከላከል ይልቅ ተቃውሞን ለመደፍጠጥ ጥቅም ላይ ሲውል በቆየው የጸረ ሽብር ህግ ነው፡፡ 

ተቃዋሚዎቹ ቢጫ እና ነጭ ካርዶችን በማሳየት ሰላማዊነታቸውን እንዲሁም እስራትና ክሱን መቃወማቸውን ሲያሳዩ ቆይተዋል፡፡ በጥቅሉ ተቃውሞዎቹ በአብዛኛው ሰላማዊ ነበሩ ሲሆኑ በአንዳንድ ቦታዎች ግን ሰላም አደፍራሽ ክስተቶች ታይተዋል፡፡ በኦክቶበር 21/2011 ተቃዋሚዎችን ከፖሊስ ጣቢያ ለማስፈታት በተደረገ ሙከራ 4 ያህል ሰዎች ሲገደሉ በአፕሪል 2012 ደግሞ ‹‹አህባሽን አላቀነቅንም›› ያለ ኢማም በመባረሩ ምክንያት በተነሳ ተቃውሞ 5 ያህል ሰዎች ተገድለዋል፡፡ 

የድርጅቱን ኮሚሽነር ቃለ መጠይቅ ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻ ይጠቀሙ፡- Samantha Schnitzer at sschnitzer@uscirf.govor (202) 786-0613.

ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው!


ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው!

ሰብአዊ መብቶቻችንን ለማስከበር ጥረት ማድረግ ከጀመርን ሰንብተናል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም እንደ አንድ አካል ሆኖ ድምጹን ሲያሰማ ወራት እንደቀልድ ነጉደዋል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ቁርጠኝነት መስፈሪያ የሆኑት ብርቅዬ መሪዎቻችንም በእስር ቤት ተከርችሞባቸው በሀሰት የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ አዎን! ዛሬም ነገም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ ብሎም ለአለም ግልጽ እንደሆነው ሁሉ መሪዎቻችን የህሊና እስረኞች ናቸው - የህዝብን ጥያቄ ለመንግስት ‹‹እናድርስ›› ባሉ ግፍ የተፈጸመባቸው መስዋእቶች! 

መስዋእትነት ዋነኛ የትግል ማእዘን መሆኑን አጥብቆ የተረዳው ሙስሊም ማህበረሰብ ገና ከጅምሩ ትግሉን ያቆም ዘንድ ይፈጸሙበት የነበሩትን ዘግናኝ የመብት ጥሰቶች መና አስቀርቷል፡፡ በከተሞችም ሆነ በገጠር ቀበሌዎች በአንድ ድምጽ ባሳየው ቁርጠኝነት የእስራት፣ የድብደባና የግድያም ሰለባ ሆኗል፡፡ ‹‹ሸሂዶቻችንን አላህ የጀነት ይበልልን!›› ብሎ እምባውን ወደአላህ ከመርጨት ውጭም አንዳችም ከሰላማዊነት የማፈንገጥ ምልክት አላሳየም - ይህ ድንቅ ሰላማዊ ትውልድ! ይህ ትውልድ ዛሬ አገር በሚያስተዳድረው መንግስት ቅንጣት ክብር ባይለገሰውም ነገ ታሪክ በገጾቹ ቀርጾ ያስቀረዋል! የፈጸመው ሰላማዊ ገድል በአለም አቀፍ የሰላማዊ ትግሎች መዝገብ ውስጥ በክብር ይሰፍርለታል! መሪዎቹ እጅግ ከስሜት የራቁና ሰላማዊ ሆነው ሳለ በግፍ መታሰራቸውን፣ ‹‹አገር እየመራሁ ነው›› ከሚለው መንግስት የተሻለ በስለው መገኘታቸውን ይመሰክራል፡፡ 

ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ መሆኑን ታሪክ ይነግረናል፡፡ አዎን! ህዝብ ዛሬም ሆነ ነገ ያሸንፋል! በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ዜጎቹ ጋር በጠራራ ጸሀይ ጦርነት የገጠመ መንግስት ዘላቂ ተጠቃሚ መሆኑን ያሳየ የታሪክ አጋጣሚ የለም! የታሪክ ገጾችን ሲበረብሩ ቢውሉ እንኳ አያገኙትም! መንግስት ወደልቦናው ይመለስ ዘንድ አሁንም ጊዜው አልረፈደም፤ ጥሪያችንም ነው፡፡

በመጨረሻም ነገ ጁሙአ ተቃውሞአችንን የምንገልጸው አንዋር መስጊድ ባለመሄድና በአካባቢያችን ባሉ ሌሎች መስጊዶች የጁሙአ ሰላትን በመስገድ ሲሆን፤ ቀጣይ የተቃውሞ መርሐ ግብሮችን አስመልክቶም ቀደም ብለን በቀጣይነት የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

Wednesday, May 02, 2012

ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ):- ለሁሉም የሰው ልጆች ምርጥ አርአያና መመሪያ

إِنَّمَا أَنتَ مُنذِرٌ وَلِكُلِّ قَوْمٍ هَادٍ [١٣:٧]
“አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ። ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።” (አል-ረዕድ 13፤7)
ይህ የነቢዩ ህይውት ድንቅ ክፍል ነው፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ለሰው ልጅ ሁሉ ምርጥ አርአያ ናቸው። መመሪያና መንገድም ጭምር። ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በፊት የተላኩ ሌሎች ነቢያት ለህዝቦቻቸው ብቻ የተላኩና መልእክታቸውም በጊዜ የተገደበ ነበር። የነቢያቶች መደምደሚያና የመጨረሻው ነብይ የሆኑት ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ለሁሉም ህዝቦችና ለሁሉም ጊዜ (እስከ አለም ፍጻሜ) በሚሆን መልዕክት ነበር የተላኩት።
በአስር የተለያዩ የቁርዐን አንቀጾች ለነቢዩ የመጣላቸው መልእክት “መመሪያና እዝነት” (ሁዳ ወራህማ)በሚል ሁለት ምርጥ ቃላት ጥምረት ተጠቅሷል። አል-አንዓም 6፡157፤ አል-አዕራፍ 7:52፣203፤ ዩኑስ 10፤57፤ ዩሱፍ 12፡111፤ አል-ነህል 16፡64፣89፤ አልነሞል 27፡77፤ ሉቅማን 31፡3፤ አል-ጃሲያህ 45፡20 መመልከት ይቻላል። እዚህ ጋ እነዚህ ሁለት ባህሪያት (መመሪያና እዝነት) (ሁዳ ወ-ራህማ) ለምን በጥምረትና በተደጋጋሚ ለነቢዩና በሳቸው በኩል ለተላከው መልእክት መገለጫ እንደሆኑ ማስተንተን ጠቃሚ ነው።
“ሁዳ” የሚለው ቃል በግርድፍ “መመሪያ” ማለት ሲሆን “ሂዳያ” ከሚለው ቃል የመጣ ሆኖ እናገኘዋለን። “ሂዳያ” መምራት እና ማሳየት የሚሉ ትርጉሞችን ይይዛል። ከዚህ በተጨማሪም “ሀዲያ” የሚለው ቃልም የዚሁ ግንድ ቅርንጫፍ ሲሆን ትርጉሙ “ስጦታ” ማለት ነው። በዚህ መሰረት “ሂዳያህ” ማለት ከአላህ ለፍጥረታቱ የተሰጠ ስጦታ ነው ማለት እንችላለን። እንደ ታዋቂው የቁርአን ተንታኝ ኢማም ራጊብ አል-ኢስፈሀኒ ገለፃ ሂዳያህ “ባማረና በመልካም ሁኔታ መንገድን ማመላከት ወይም ወደ ሚፈለገው መምራት” ማለት ነው። ይህ ማለት ማብራራትና ማመላከት (አል-ኢርሻድ ወል ደላላህ) ወይንም ወደሚፈለገው ዓላማ ይደርስ ዘንድ መርዳትና መደገፍ ብሎም ማስቻል (አተውፊቅ ወል ኢልሀም) ማለት ነው። የመጀመርያው የነቢያትና የደጋጋ የአላህ ባርያዎች ስራ ሲሆን ሁለተኛውን የአላህ ብቻ የተተወ ነው። በሌላ በኩል “ራህማ” የሚለው ቃል “እዝነት፣ ፍቅርና ርህራሄ” ማለት ሲሆን በቁርዐን ውስጥ “አል-ራህማን እና አል-ረሂም” (ሩህሩህና በጣም አዛኝ) የሚሉት ስሞች በተደጋጋሚ ተጠቅሰዋል፤ ነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ “ራህመትን ሊል አለሚን” (የአለማት እዝነት) ተብለዋል።
የነዚህ ቃላት (መመሪያና እዝነት) ጥምረት የሚፈጠረው ትምህርት በሁለት መልኩ ይታየል። የመጀመሪያው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት እውነት፤ ትክክለኛና ፍትሀዊ መሆኑንና መልዕክቱ ዋነኛ የእዝነትና የርህራሄ መልዕክት መሆኑን ያስረዳል። መልዕክቱ ከቸጋራነትና ሻካራነት በራቀ መልኩ ገርና በምህረቱ የተከሸነ ነው።በሁለተኛ ደረጃ ይህ በነቢዩ በኩል የመጣው መልእክት በዚች አለም ለቀን ተቀን ህይወታችን መመሪያ እንዲሆንና የአላህ ምህረት እንድናገኝ እንዲሁም በመጪው አለም ስኬትና መድህን እንድናገኝ የሚያደርግን ሁነኛ መሳረያ ነው።
የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምራቻ (guidance) ሶስት ባህሪዎችን በትኩረት እንቃኝ፡-
1.ሁሉንአቀፍ
2.እዝነት የተሞላበት
3.አለም አቀፋዊ
1.ሁሉንአቀፍ
የነቢዩ መንገድ ሁሉን አቀፍ ነው ስንል ሁሉንም የህይወት መስኮችን ያካተተና ሁሉንም የተስተካከለና ያማረ ያደርጋል ማለት ነው። መመሪያው ትክክለኛ እምነትን፤ የተስተካከለ የአምልኮ መንገድን፤ ምርጥ ስነ-ምግባርን፤ የተቃና የግብይት ስርዓትን፤ ከቤተሰብ ጋር ያለ ግንኙነት፤ከወዳጅና ጠላት ጋር የሚኖርን ግንኙነት ሁሉ ይዳስሳል። ባጠቃላይ እንደ ግለሰብና እንደ ማህበረሰብ ሊኖረን የሚገባውን ሚና አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም ነገር ሚዛናዊና ገር በሆነ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት እናገኛለን። በዚህ መስክ የነቢዩን አጠቃላይ የህይወት መመሪያ ሰብስቦ የዘገበውን የታላቁን የኢስለም ሊቅ የኢብነል ቀይም ስራ የሆነውንና በስድስት ጥራዝ የተዘጋጀውን “ዛዱል ሚዓድ ፈሀድይ ኸይረል ኢባድ” ማየት ያሻል። ፀሀፊው ከግል እስከ ህብረተሰብ ባሉ ዝርዝር የህይወት መስኮች ከነቢዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) ህይወት ምሳሌ በማጣቀስ ያቀርባሉ።
2.እዝነት የተሞላበት
ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልካምና ገር መምህር ነበሩ፤ አስቸጋሪና ግትር አልነበሩም። ሁልጊዜም ለባልደረባዎቻቸው በንፁህና ገር (ሀነፊየቱ-ሰምሀእ) በሆነ ቅን መልዕክት የተላኩ እንዳሆኑ ያስተምሩ ነበር (ሙስነድ አህመድ 21916)። ሰዒድ ኢብኑ ቡርዳህንና ሙዓዝ ኢብኑ ጀበልን ወደ የመን በላኩ ወቅት ያሉትን እንዲሁ እናስታውስ፡-
يسرا ولا تعسرا وبشرا ولا تنفرا وتطاوعا  (البخارى (
“አግራሩ አታካብዱ አበስሩ አታስደንብሩ በጋራም ስሩ።” (አል-ቡኻሪ)
ከነብዩ መልካም የማስተማሪያ ስልቶች አንዱ ባልደረቦቻቸውን በሁሉም ጊዜ የሚገስፁና የሚያስተምሩ አልነበሩም፤ ይልቁንስ ቦታና ጊዜ እንዲሁም አጋጣሚዎችን በመምረጥና በመጠቀም ያስተምሩ ነበር።
ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ:-
كان النبي- صلى الله عليه وسلم- يتخولنا بالموعظة في الأيام؛ كراه السآمة علينا. (البخارى(
“ነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እኛን በማስተማሩ ሂደት እንዳንሰላች አመች ጊዜ ፈልገው ይጠቀሙ ነበር” (አል-ቡኻሪ)
3.አለም አቀፋዊ
የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት አለም አቀፋዊ ነው። በአንድም መልዕክታቸው ላይ ለአረቦች ወይንም በጊዜው ለነበሩት ሰዎች ተብሎ የተተው ነገር የለም። ቁርአን የፈቀደው ነገር በማንኛውም ጊዜ ለሁሉም ሰው ጠቃሚና መልካም ሲሆን የከለከላቸው ነገሮችም እንዲሁ በማንኛውም ጊዜና ለሁሉም ሰው ጎጂና መጥፎ ናቸው። በየትኛውም ዘመን ያሉ ሰዎች የነብዩን መልዕክት ቢጠቀሙበት ውጤታማ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም። ከዚህም ሁሉ ጋር ግን ነቢዩ በፍፁም እምነቱን በሌሎች ላይ በግድ አልጫኑም ነበር። ቁርዐን በሀይማኖት ማስገደድን በጥብቅ ከልክሎታል (አል-በቀራህ 2፤256)::
ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሰው ልጅን መንገድ በማሳየት በኩል የተሳካላቸው ነበሩ። ነቢዩን አላህ መርጦ መልዕክቱን ሲሰጣቸው በጊዜው የነበሩት ብቸኛ ሙስሊም እርሳቸው ብቻ ነበሩ። ከብዙ ድካም፤ ልፋትና፤ ህመም በኋላ በአላህ ፍቃድ ትውልድን አቀኑ፤ ብሎም ሌሎችን ሊመሩና ምሳሌ ሲሆኑ የሚችሉ ሰዎችን አፈሩ፤ ተከታዮቻቸውን አንዲትን የእርሳቸውን መልዕክት በአግባቡ የተረዳ ሰው ያስተምር ዘንድ ሰበኩ፤ በሀያ ሶስት ዓመት ውስጥ መልዕክቱ መላውን አረቢያ አዳረሶ ወደ ውጪ ወጣ። ሰዎች በገፍ ወደ እምነቱ ይጎርፉ ጀመር። በስልሳ ሶስት ዓመታቸው ከዚህች ዓለም ሲለዩ የአረቢያን ሙሉ በሙሉ ቀያይረዋት ነበር። የተሟላ እምነት፤ የተጠናከረ መንግስት፤ የተቀናበረ የትምህርትና የእውቀት ስርዓት፤ የተቃና ስነ-ምግባርንና ምርጥ ስብዕናን አሰፈኑ ብሎም ላማረ ስልጣኔ መሰረት ጣሉ። የአላማ ሰዎችንና ለሰው ልጅ ቅኑን መንገድ የሚያመላክቱ ህዝቦችን አበጁ። ከኢስላም በፊት ወና የነበረው ታሪካቸውን በብርሀናማ ገድሎች አሳመሩት፤ በተዋቡ የስልጣኔ እርከኖች አሸበሩቁት።
እጅግ ብዙ ተንታኞች፤ የታሪክ ተመራማሪዎችና ፊላስፎች ይህንን አለምአቀፍ፣ ሁለንተናዊና ስኬታማ የሆነውን የነቢዩን ተልዕኮ እውነታ አፅድቀዋል። ድንቅ ኢንጊሊዛዊ ፀሀፊ ጆርጅ በርናንድ ሾው እንዲህ ይላሉ:- “ሁሌም የሙሀመድን እምነት የምሰጠው ቦታ እጅግ የላቀ ነው፤ ይኸውም ከምርጥ መገለጫዎቹ የመነጨ ነው። ይህ እምነት ከየትኛውም የአለም ተለዋዋጭ መልክ ጋር በየትኛው ቦታና ጊዜ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ብቸኛው እምነት ነው። ስለዚህ ድንቅ ሰው (ሙሀመድ) በጥልቀት አጥንቻለሁ በኔ አመለካከት ‘የክርስቶስ ጠላት’ ከመባል እጅግ የራቀና ይልቁንም ‘የሰው ልጅ አዳኝ’ ሊባል ይገባዋል።” (ዘ ጄኒዩን ኢስላም ጥራዝ 1፣ ቁ.8፤ 1936)
አሜረከዊው የታሪክ ሰው ማይክል ሀርት በታሪክ የታዩና ተፅዕኖ ያሳደሩ የአለምን ምርጥ ሰዎች ከደረጃ ባስቀመጡበት “ዘ 100፡ ኤ ራንኪንግ ኦፍ ዘ ሞስት ኢንፉሌንሺያል ፐርሰን” በተሰኘው መፅሀፍ ለምን ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያው ደረጃ እንደሰጣቸው ሲናገር እንዲህ ይላል:-
“በእርግጥ በታሪክ የአለማችን ምርጥና ታላቅ ተፅዕኖ ያሳደሩ ሰዎች ተርታ ለሙሀመድ አንደኛ ደረጃ መስጠቴ አንዳንድ አንባቢዎችን ሊያስገርምና ሌሎችን ሊያጠያይቅ ይችል ይሆናል። ሆኖም ግን በአለማዊው ሆነ በሀይማኖታዊው ዘርፍ ሙሉ በሙሉ የተሳካላት ብቸኛ ሰው ሙሀመድ ነው።” (ዘ 100፡ ኤ ራንኪንግ ኦፍ ዘ ሞስት ኢንፉሌንሺያል ፐርሰን፤ ኒዮርክ፤1978፣ ገፅ 33)
ይህን መመሪያ በአግባቡ ተከትለን መተግበሩ የወቀቱ ጥያቄና የእኛ ስራ ነው። እነዚያ ቀደምት አባቶቻችን የነበሩበትን የብርሀን ዘመን ላይ ለመድረስ ካለንበት የችግርንና የሰቆቃ አረንቋ ለመውጣት የዚህን ዓብይ ምሳሌ መስመር በመስመር ልንከተል ግድ ይላል።
ሁላችንንም አላህ ይርዳን አሜን!!

ብሄራዊ ባንክ ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ባንኮች አይቋቋሙም አለ

ሁሉም የንግድ ባንኮች የተጠቃሚዎችን ፍላጐት እያከበሩ ይሠራሉ እንጂ፣ የክርስቲያንም ሆነ የሙስሊም ተብለው የሚቋቋሙ ሃይማኖታዊ ባንኮች እንደማይኖሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡  ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ባለፈው ሳምንት ዳያስፖራውን ባነጋገሩበት ወቅት፣ በሰሜን አሜሪካ ከዳያስፖራው ጋር የተደረጉ 17 ስብሰባዎችን መካፈላቸውን በመጥቀስ፣ መድረኩን ሲመሩ ለነበሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጥያቄ ያቀረቡ ግለሰብ፣ ‹‹እናንተ የተጠየቃችሁትን አትፈጽሙም፤ አገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው ይባላል፡፡ የዘምዘም ባንክ ምሥረታ ለምን ተቋረጠ? በገንዘብ በኩል የሙስሊሙ ሕዝብ ተሳትፎ ለምን እንዲጠናከር ጥረት አታደርጉም?›› ብለው ነበር፡፡
ለጥያቄው መልስ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ዮሐንስ አያሌው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖትን መሠረት አድርጐ የሚቋቋም ባንክ እንደማይኖር በመግለጽ፣ ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋምን በተመለከተ በወጣው መመርያ መሠረት ባንኮች በሙሉ አገልግሎቱን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡
ከወለድ ነፃ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ የማኅበረሰብ ክፍሎችም በሁሉም ባንኮች በተዘጋጁ መስኮቶች ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉና ባንኮችም አገልግሎቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አቶ ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡
ከወለድ ነፃ የሆነ ባንክ ለማቋቋም በምሥረታ ላይ የነበረው የዘምዘም ባንክ አደራጆች በወቅቱ መመርያ ባለመኖሩ ብሔራዊ ባንክን ጠይቀው ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ መመርያ አውጥቶ ነበር፡፡ ዘምዘም ባንክም የረቂቅ መመርያውን መውጣት ተከትሎ ወደ አክሲዮን ሽያጭ በመግባት የመጀመርያ ጠቅላላ ጉባዔውንም ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በምሥረታ ላይ የነበረው ዘምዘም ባንክ ጠቅላላ ጉባዔውን ቢያደርግም፣ በብሔራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋምን አስመልክቶ የወጣው የመጨረሻው መመርያ በምሥረታ ላይ የነበረው ባንክ ሥራውን እንዳይቀጥል አድርጐታል፡፡
በወቅቱ ብሔራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ ራሱን የቻለ ባንክ በኢትዮጵያ ማቋቋም እንደማይቻል፣ ሁሉም ባንኮች ግን ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡበት መስኮት እንደሚያደራጁ መግለጹን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በብሔራዊ ባንክ ውሳኔ መሠረት በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ባንኮች ስለማይመሠረቱ፣ ተገልጋዩ ኅብረተሰብ በተለያዩ ንግድ ባንኮች ውስጥ በመረጡት መንገድ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአርሲ በፖሊስና በህዝቡ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አራት ሰዎች ተገደሉ


በ ሔኖክ ሰማእግዜር ፈንቴ | ዋሽንግተን ዲሲ

በምእራብ አርሲ ዞን አሳሳ ከተማ የዓርብ ጸሎት አድርሰው ከመስጊድ በሚመለሱ ሰዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያስ 4 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲመሩ የነበሩ አንድ የአሳሳ ከተማ ነዋሪን የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሲያውሉ፤ ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት በሰው ላይና በንብረት ጥፋት ደርሷል ብሏል።
በስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው፤ ለምን እንደሚታሰር፤ ከታሰረም መብቱ ተጠብቆ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመራ፤ ወይም የአካባቢው ማህበረሰብ ለህግ እንዲያቀርብ በጠይቁ ጊዜ ፖሊሶች ሁኔታውን ባለመቀበል ሰውየውን ሲያስሩ፤ ማህበረሰቡ በቁጣ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን ይገልጻሉ። ለዚህ ቁጣ የፖሊስ አጸፋዊ ምላሽ ጥይት በቀጥታ ውደ ሰዎች መተኮስ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ አዛዥ አቶ ደበሌ አዱኛ የእስልምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የጅሃድ ጦርነት ሲቀሰቅስ የነበረ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ፤ ጥቂት ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት 4 ሰዎች መገደላቸውንና 10 ፖሊስ መቁሰሉን አቶ ደበሌ የመንግስቱ ልሳን ለሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ከሰላማዊ ሰዎች የቆሰለውን ቁጥር ይፋ አላደረጉም።
“ይሄ ቡድን የሚያራምደው ሃይማኖት አይደለም፤ በሃይማኖት ሽፋን ድብቅ የፖለቲክ አጀንዳ ያለው ነው። ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ያረጋገጠውም የግለሰቦቹ አላማ ይች አገር የተያያዘችውን የልማትና የእድገት ጉዞ ማደናቀፍ ነው” ብለዋል።
አቶ ደበሌ አክለውም በአሳሳ በተቀሰቀሰው ሁከት የህዝብ አገልግሎቶች ማለትም የስልክና የፖስታ ቤት ህንጻዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል ያላቸውን ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጸዋል።

Tuesday, April 17, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ንግግር በትዝብት መነፅር


ጥያቄውን እንዲያቀርብ ተፅፎ የተሰጠው የፓርላማው ወንበር አሟቂ ‹‹በአሁኑ ሰዓት ፅንፈኝነትና አክራሪነት እየተበራከተ ቀድሞ የነበረ የመቻቻል ባህላቸንን…..ምናምን ብሎ ብዙ ካወራ በኋላ ‹‹መንግስት ህገመንግስት ለማስተማር ባደረገው ጥረት ጣልቃ ገባህ እየተባለ ነው›› ሲል ለምን የመንግስታችን ድብቅ ሴራ በአደባባይ ተወራ› በሚያስመስል መልኩ ተጨማሪ አውርቶ ‹የመንግስት አቋም ምንደን ነው› ሲል ጠየቀ፡፡1. ጠቅላይ ሚኒስትሩም የወትሮው ‹ብቃታቸው› ባልታየበት መልኩ በማይጥም ተረት ተረት ንግግራቸውን ጀምረው አስገራሚ ወሬዎችን አስደመጡን2. ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሙስሊም መቶ በመቶ ሱፊ ነው ሲሉ የተደመጡት አላህ ሙስሊሞች ብሎን ሲያበቃ የመንግስትዎ ስልጣን ይህን ሰያሜ የማስቀየር መብት ያለው መስሎዎት ይሆን
3. ሱፊ፤ ሰለፊ ማለትስ ምን እንደሆነ አውቀውት ነው በእምነት ነክ ጉዳዮች ከዚህ በፊት የሰለቸንን የፖለቲካ መሪ ሃይማኖታዊ ትንታኔ የሰጡን; ደግሞስ በየትኛው ሳይንሳዊ ጥናት ተሞርኩዘው ነው መቶ በመቶ በሚል ድፍረት የደመደሙት፡፡ ይህ ንግግርዎ ከዚህ የቀደሙትንም ሆነ የሚከተሉትን ንግግርዎን እንዳናምናቸው ያደርገናል፡፡
4. ነባሩ የእስልምና አይነት እያሉም ተደምጠዋል፡፡ ልክ ለእምነታችን የተቆረቆሩልን በማስመሰል፡፡ ቀድሞ እስልምና አንድና አለምአቀፋዊ ነው፡፡ በዘመንም ሆነ በሃገር የማይለዋወጥ አንድ እምነት፡፡ በየዘመኑ ጠላቶች የሚነሱበትም ለነሱ ርካሽ ፖለቲካ በሚሆን መልኩ በርዘውና ከልሰው እንደ አዲስ ሊፈጥሩት ሲሞክሩ ስላልተሳካላቸው ነው፡፡ ስለቀድሞ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለማውራት ከሆነ ደግሞ የቀደምት ሙስሊሞቻችንን አቋም የምንኮራበት እንጂ የምናፍርበት አይምሰሎት፡፡ ባይሆን እንደነሱ ለመሆን ቢሳካለን እንጥራለን እንጂ፡፡ የኢትዮጵያ ነባሮቹ ሙስሊሞች እኮ እነ ጠለሃ ጃዕፈር፤ እነ አባ ጅፋር እነ ሃሰን አንጃሞ እና ጠርተን የማንዘልቃቸው ለጠላት ሴራ የማይንበረከኩ ጀግኖች ነበሩ፡፡
5. እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሌሎች ሚኒስትሮቻቸው በእውቀትና በመረጃ እንደሚበልጡ ለማስመስከር ለየት ያለ አቋም ይዘው መቅረብ ይወዳሉና ‹‹ ወሃብያ የሚለው መጠሪያ ትክክለኛና አግባብ ላይሆን ይችላል›› ሲሉ ሰማናቸው፡፡ በእርግጥ እርሳቸውም ደግመው ወሃብያ ቢሉን እምነታችንን ለአደጋ አንድነታችንን ለጠላት አሳልፈን ከመስጠት ሞትን እንደምንርጥ ሳያውቁት አይቀርም፡፡
6. ዋናውና ትልቁ ነገር ግን ጠያቂውም ጠይቅ የተባለው ስለ ምናባዊ ፅንፈኞች እንጂ ስለተጨባጩ የኛ የሙስሊሞች ጥያቄ አይደለም እርሳቸውም የመለሱት የኛን ጥያቄ አይደለም፡፡ ባይሆን የአብደላህ አልሃረሪንና የአህባሽን ስም ሲጠሩ የአብሮአደግ ጓደኞቻቸውን ስም ሊጠሩ በሚችሉበት ብቃት መሆኑ ጉዳዩን ከዚህ በፊት ከዘባረቁት ባለስልጣኖቻቸው ይልቅ እርሳቸው በባለቤትነት እንደያዙት መገመት አይከብድም፡፡
7. ከዚህ በፊት ከበቂ በላይ በሆነ መረጃ ‹አዎ አህባሽን አምጥተናል› የሚሉ የባለስልጣኖቻቸውን ንግግር ለምናውቀው ሙስሊሞች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹እኛ ጣልቃ አልገባንም› ዳግም ሽሽት ‹እኔ ሳልሆን ባለስልጣናቶቼ ተሳስተው ነው› ከሆነ ትርጉሙ እርሶዎን እንድናምን ጣልቃ መግባታቸውን ያመኑትን ሹመኞች መሰዋዕት ያድርጉ፡፡ የሚያዋጣ ይመስላል፡፡ አሊያማ በአንድ መንግስት ውስጥ እንዴት አስር ቃል ይነገራል፡፡
3. ሱፊ፤ ሰለፊ ማለትስ ምን እንደሆነ አውቀውት ነው በእምነት ነክ ጉዳዮች ከዚህ በፊት የሰለቸንን የፖለቲካ መሪ ሃይማኖታዊ ትንታኔ የሰጡን; ደግሞስ በየትኛው ሳይንሳዊ ጥናት ተሞርኩዘው ነው መቶ በመቶ በሚል ድፍረት የደመደሙት፡፡ ይህ ንግግርዎ ከዚህ የቀደሙትንም ሆነ የሚከተሉትን ንግግርዎን እንዳናምናቸው ያደርገናል፡፡4. ነባሩ የእስልምና አይነት እያሉም ተደምጠዋል፡፡ ልክ ለእምነታችን የተቆረቆሩልን በማስመሰል፡፡ ቀድሞ እስልምና አንድና አለምአቀፋዊ ነው፡፡ በዘመንም ሆነ በሃገር የማይለዋወጥ አንድ እምነት፡፡ በየዘመኑ ጠላቶች የሚነሱበትም ለነሱ ርካሽ ፖለቲካ በሚሆን መልኩ በርዘውና ከልሰው እንደ አዲስ ሊፈጥሩት ሲሞክሩ ስላልተሳካላቸው ነው፡፡ ስለቀድሞ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለማውራት ከሆነ ደግሞ የቀደምት ሙስሊሞቻችንን አቋም የምንኮራበት እንጂ የምናፍርበት አይምሰሎት፡፡ ባይሆን እንደነሱ ለመሆን ቢሳካለን እንጥራለን እንጂ፡፡ የኢትዮጵያ ነባሮቹ ሙስሊሞች እኮ እነ ጠለሃ ጃዕፈር፤ እነ አባ ጅፋር እነ ሃሰን አንጃሞ እና ጠርተን የማንዘልቃቸው ለጠላት ሴራ የማይንበረከኩ ጀግኖች ነበሩ፡፡5. እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሌሎች ሚኒስትሮቻቸው በእውቀትና በመረጃ እንደሚበልጡ ለማስመስከር ለየት ያለ አቋም ይዘው መቅረብ ይወዳሉና ‹‹ ወሃብያ የሚለው መጠሪያ ትክክለኛና አግባብ ላይሆን ይችላል›› ሲሉ ሰማናቸው፡፡ በእርግጥ እርሳቸውም ደግመው ወሃብያ ቢሉን እምነታችንን ለአደጋ አንድነታችንን ለጠላት አሳልፈን ከመስጠት ሞትን እንደምንርጥ ሳያውቁት አይቀርም፡፡6. ዋናውና ትልቁ ነገር ግን ጠያቂውም ጠይቅ የተባለው ስለ ምናባዊ ፅንፈኞች እንጂ ስለተጨባጩ የኛ የሙስሊሞች ጥያቄ አይደለም እርሳቸውም የመለሱት የኛን ጥያቄ አይደለም፡፡ ባይሆን የአብደላህ አልሃረሪንና የአህባሽን ስም ሲጠሩ የአብሮአደግ ጓደኞቻቸውን ስም ሊጠሩ በሚችሉበት ብቃት መሆኑ ጉዳዩን ከዚህ በፊት ከዘባረቁት ባለስልጣኖቻቸው ይልቅ እርሳቸው በባለቤትነት እንደያዙት መገመት አይከብድም፡፡7. ከዚህ በፊት ከበቂ በላይ በሆነ መረጃ ‹አዎ አህባሽን አምጥተናል› የሚሉ የባለስልጣኖቻቸውን ንግግር ለምናውቀው ሙስሊሞች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹እኛ ጣልቃ አልገባንም› ዳግም ሽሽት ‹እኔ ሳልሆን ባለስልጣናቶቼ ተሳስተው ነው› ከሆነ ትርጉሙ እርሶዎን እንድናምን ጣልቃ መግባታቸውን ያመኑትን ሹመኞች መሰዋዕት ያድርጉ፡፡ የሚያዋጣ ይመስላል፡፡ አሊያማ በአንድ መንግስት ውስጥ እንዴት አስር ቃል ይነገራል፡፡

እኛ ሱፊይ ሰለፍይ ወሀብይ አይደለንም አላህ ለኛ የመረጠልን ሙስሊም የሚለውን ስም ነው ሌላ ስም አትስጡን አሸባሪዎች አክራሪዎች አይደለንም የሐገራችንን እድገት የምንፈልግ ሰላማዊ ሙስሊሞች ነን ሀስቡን አላህ ወኒዕመል ወኪል!

ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ስለ አህባሽ በፓርላም ተናገረ

prim minister meles  
መለስ ዜናዊ ብቻውን በሚያስተዳድረው ፓርላማ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ በራሳቸው መንገድ ተርጉሞታል በንግግሩ ውስጥ በተደጋጋሚ ሲያነሳው የነበረው አንዱን ሱፊያ አንዱን ሰለፍያ እያለ መከፋፈል ነው የማከረው በተጨማሪ ምንም በማይገናኝ መልኩ የኛን ጥያቄ በአሁን ጊዜ እንደ ግብፅ የመን ቱኒዚያ ሊቢያ ከመሳሰሉት ሀገሮች ጋር በማገናኘት እስላማዊ     

የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት ለሚከተሉት እምነት እላፊ ድጋፍ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩ ተገለፀ


አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 8/2004 የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት በሚከተሉት እምነት በመንግስት በህዝብ በተሰጣቸው ኃላፊነት መካከል የሚወራውን ድንበር በማለፍ እላፊ ድጋፍ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩን አንድ ሰነድ አመለከተ፡፡ በሰላምና በህገ መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትን ግዴታም ነው በሚል ርዕስ በቅርቡ በኢህዴግ ፅ/ቤት የወጣው ሰነድ እንዳመለከተው የድርጅቱ አመራሮችና አባላት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ለሚከተሉት እምነት እላፊ ድጋፍ ሲሰጡ የሚታዩበት ሁኔታ በርካታ ነው፡፡ እንደ ማሳያም በአንዳንድ አዓላት ሀገሪቱን የኃይማኖቶች መቻቻልና መከባበር ሳይሆን የፉክክርና የፍጥጫ ማዕከል እንደሆነች በሚያስመስል መልኩ ድጋፍ ሲሰጡ ይታያል ነው ያለው ሰነዱ፡፡ የጋራ የሆኑ የመንግስት አደባባዮች፣ቢሮዎች፣የሌላ ኃይማኖት ተከታይ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችና አጥሮች ጭምር በአንድነት ምልክቶችና የሌላውን እምነት በሚነካኩ እንዲሁም ህገመንግስቱና የሰንደቅ ዓላማ በሚፃረር መልኩ ሲንፀባረቁ የሚተባበሩበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ ሰነዱ በእነዚህ ድርጊቶች ተባባሪ ከሆኑና በመጠኑ የተሸሉት ብሎ የጠቀሳቸው ደግሞ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ሳያስተካክሉ አጥር ጥግ ቆመው የሚመለከቱትን አመራሮችና አባላትን ነው፡፡ እናም አብሮ ማጥፋትና ሌላው ሲያጠፋ እያዩ እንዳላዩ ማለፍ ስህተት ነው ያለው ይኼው ከኢህአዴግ ጽ/ቤት የወጣው ሰነድ በሁለቱም መንገድ ጥፋቶቹ ከመፈፀም የሚገቱበት ሁኔታ አንደማይኖርም አመልክቷል፡፡ ሙስሊምና ክርስቲየን የሆኑ የኢህዴግ አባላትና አመራሮች ይህን ተከተሉ ያን አትከተሉ የሚባሉበት ሁኔታ እንደሌለም ገልፀዋል፡፡ በዚህ ረገድ ችግሩ የሚስተዋለው ከሚከተሉት እምነት ወይም የእምነት ቡድን (ሴክት) ውስጥ መቻቻልን ህገመንግስቱን የሚሸረሽሩ አዝማሚያዎች ሲንፀባረቁ ከድርጅቱ መርህና ከሀገሪቱ ህገመንግስት መንፈስ አንፃር በጥብቅ ዲሲፕሊን የማይታገሉ መሆናቸው እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ የኢህአዴግ አባል የእምነት ነፃነት አለው ሲባል ፀረ ህገመንግስት አቋሞችን የሚያራምድ ድርጅት ወይም በኃይማኖት ሽፋን በሚያስኬድ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ አለበት ማለት አለመሆኑን አስረድቷል፡፡ በመሆኑም በኢህዴግ አባላትና አመራሮች አቋማቸውን ሳያስተነትኑ ከሚከተሉት እምነት መሰረታዊ አስተምህሮት ፈንጠር ያሉና ፀረ ህገመንግስታዊ መግለጫ ያላቸው አቋሞችን ተላብሰው ይታያሉ ነው ያለው ሰነዱ፡፡ በዚህም መሰረት አንዳንድ የኢህዴግ አባላትና አመራሮች ኢህዴግነትንም ፀረ-ኢህአዴጋዊ አቋሞች የያዙ ቡድኖችንም የሚያንቀሳቅሱበት ሁኔታ በገሃድ እንደሚታይ ነው ሰነዱ ይፋ ያደረገው፡፡ ስለሆነም ከዚህ አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ግልፅነት በመፍጠር የአባላቱንና አመራሮቹን አሰላለፍ ማስተካከል እንደሚገባ ለማስተካከል የሚቸገር ደግሞ ከድርጅቱ መፅዳት እንዳለበት ነው ያመለከተው፡፡ ህገ መንግስቱ በኃይማኖት ዙሪያ ካስቀመጣቸው መርሆሆች በመነሳት በአባሉና አመራሩ ዘንድ የጋራ ግንዛቤ መፍጠርና ትግሉም ይህንኑ መሰረት ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቅሷል፡፡ ህገ መንግስቱ ለግለሰብና ለቡድን መብቶች አስተማማኝ ጥበቃ የሰጠውን ያህል መብቶችን ለመተግበር የሚደረጉ እንቅስቃሰሴዎች መከተል የሚገቡ መርሆዎችና ዳር ድንበሮች በዝርዝር እንዳስቀመጠም ጠቅሷል ከኢህአዴግ ፅ/ቤት ለድርጅቱ አመራሮችና አባላት መወያያነት በቅርቡ የወጣው ይህው ሠነድ፡፡

Sunday, April 08, 2012

አስሩ ትዕዛዛት

አስሩ ትዕዛዛት፤ ሁሉን አቀፍ መልዕክት

በሱረቱል አንዓም የቁርአን አንቀፅ 151-153 ውስጥ አስር ድንቅ ጠቅላይ ትዕዛዛትን እናገኛለን። ስለ እነዚህ ትዕዛዛት ኡባዳህ ኢብን ሳሚት (ረ.ዐ) የተባለው የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሰሀባ ሲናገር እንዲህ ይላል “ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ሰዎች ጋር ኢስላማዊ ቃል-ኪዳን ሲገቡ እነዚህ አንቀፆችነቡ ነበር
አንቀፆቹን እንመልከት፡-
قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُم مِّنْ إِمْلَاقٍ نَّحْنُ نَرْزُقُكُمْ وَإِيَّاهُمْ وَلَا تَقْرَبُوا الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ ﴿١٥١﴾ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ وَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ لَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا وَإِذَا قُلْتُمْ فَاعْدِلُوا وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ وَبِعَهْدِ اللَّهِ أَوْفُوا ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ ﴿١٥٢﴾ وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ ﴿١٥٣﴾ [٦:١٥٣-١٥١]
“ኑ ጌታችሁ በናንተ ላይ እርምደረገውን ነገር (በርሱምዘዛችሁን) ላንብብላችሁ በላቸው፤ በርሱ (በአላህ) ምንንም አታጋሩ፤ ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ) ልጆቻችሁንም ድህነት ፈርታችሁ አትግደሉ፤ እኛ እናንተንም እነሱንም እንመግባችኋለንና፤ መጥፎ ሥራዎችንም ከርሷ የተገለጸውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡችንም አላህ እርምደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጂ አትግደሉ፤ ይሃችሁ ታውቁ ዘንድ (አላህ) በርሱ አዘዛችሁ።
የየቲምንም ገንዘብ አካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ በዚች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፤ ሥፍርንና ሚዛንንና በትክክሉ ሙሉ፤ነፍስን በችሎታዋ እንጂ አናስገድድም፤ በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም (እውነትን በመናገር) አስተካክሉ፤ በአላህም ቃልኪዳን ሙሉ ይኻችሁ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፤
ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው ተከተሉትም (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፤ (ከቀጥተኛው) መንገድ እናንተን ይለዩዋችኋልና ይኻችሁ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ።” (አል- አንዓም 6፡151-153)
አንዳንድ የኢስላም አዋቂዎች እነዚህን አንቀፆች “አዲኑል ጃሚእ” በማለት ይጠሯቸዋል፤ ጠቅላላና ሁሉን አቀፍ የሐይማኖች ትምህርቶች ማለት ነው። እነዚህ ትዕዛዛትን አስተሳሰብን፣ አምልኮን፣ ግብረ ገብነትንና ማህበረሰባዊ፣ ሥነ-ዜጋዊና፣ ኢኮኖሚዊ ህግጋትንዘሉ ናቸው። እነዚህኑ የመሳሰሉት ትምህርቶችና በተውራት (ኦሪት) ዘፍጥት (20፡ 2-17) እና ዘዳግሞ (5፡6-21) ተፅፈው እንመለከታለን:: እነዚሁ ትዕዛዛት ለኢስራኤል ልጆች የወረዱ የነበሩ ሲሆን አስርቱ ትዕዛዛት በመባልም በህዝብ ክርስቲትና አይሁድ ዘንድ ይታወቃሉ። በዚህም መልኩ ይጠቃለላሉ።
  1. ከኔ ከአምላክህ ሌላ አምላክ አይኑርህ
  2. ለኔም ምስሎችን አታድርግ
  3. የጌታህ ሥም በከንቱ አትጥራ
  4. ሰንበት አታፍርስ
  5. ወላጆህን አታዋርድ
  6. አትግደል
  7. ዝሙት አትፈጽም
  8. አትስረቅ
  9. በሐሰት አትመስክር
  10. የራስህልሆነን አትመኝ
እነዚህ ትዕዛዛት በቁርኣን ውስጥ በሦስት የአል-አንዓም ምዕራፍ አንቀፆች ውስጥ ተወስተዋል። እንዳንዱ አንቀፅ ግሩም የሆነ የማሰሪአንቀፆች ተጠቅሞም እንመለከታለን። በመጀመሪው አንቀፅ ውስጥ የሚገኙት አምስት ትዕዛዛት “ትገነዘቡ ዘንድ” በሚለው ሲዘጋ ሁለተኛው አንቀፅ ሥር የሚገኙትን አራት ትዕዛዛት ደግሞ “ታስታወሱ ዘንድ” በሚል ሀረግ ሲዘጉ እንመለከታለን። እንዲሁም አንድ ትዕዛዝንዘለው የመጨረሻው አንቀጽ “ፈጣሪችሁን ታውቁ ዘንድ” በሚል ሐረግ ተቋጭቷል። በቀላሉ ስንጠቀልለው ምክንታዊ ሆናችሁ ስታስታውሱና ስትረዱ ብሎም ሰማዊውን መንገድ ስታስታውሱና ስትከተሉ ፈጣሪን ትረዳላችሁ፤ ቀጥተኛውንና አላህን የሚፈሩትን ሰዎች መንገድ ትከተላላችሁ። ተቀዋንም ትላበሳላችሁ። ይህም የእምነትንና የመጨረሻ ግብ ነው። እስቲ ሶስት ክፍሎች እንመልከት።
  1. I.ማስተዋልን ትላበሱ ታስተነትኑና ትረዱም ዘንድ በእርግጥ ታዘዛችሁ፤
    1. 1.አንድም አካል ከአላህ ጋር አታጋሩ:- በእርግጥምለው አንድ አምላክ ብቻ ነው። ከአላህ ውጪ ለአምልኮ የምናጋርው አካል ካለ “ሽርክ” ውስጥ ወድቀናል። የኃጢት ሁሉ ቁንጮንም ፈፀመናል። በተውሂድ ማመን፤ ከአላህ ውጪ ማመንም አለመገዛት አዕምሮ ሊቀበል የሚችለው ድንቅ መርህ ነው። በየትኛውም አቅጣጫ ብንመለከት ከአንድ በላይ አምላክ አለ ማለት ከአዕምሮ ምክንታዊ ፍጥረት ጋር ይጋጫል። አስተሳሳባዊ ሰላም ይነሳል። የአመክንዮ (logic) ህግንፋልሳል። ከአንድ በላይ አምላክ አለ በሚሉት ወገኖች ዘንድም የምንመለከተው የዚህ አይነቱን መፋለስ ነው።
    2. 2.ለወላጆችህ ቅን ሁን፡- በዚህ ገለፃ ውስጥ አላህ የተጠቀመው “ኢህሳን” የሚለውን የአረብኛ ቃል ሲሆን ይህም ሁሉን አቀፍ መልካም ተግባራትን ባማረ ሁኔታ ለአላህ ብሎ መወሰንንመለክታል። በእርግጥ አዕምሮው በትክክል የሚሠራ ሰው ወላጆቹን ስለከፈሉት መስዋዕትነት፤ ለማሳደግ ሲሉ ስለተወጡት የህይወት ስንክሳር፣ ስለ ተጋፈጡት የመከራ ጋራ ሲልከብራል፤ልቃል፤ ከፍተኛ ደረጃን ይለግሳል፤ በእዝነትና ርህራሄ ይቀርባል። ባረጁና እርዳታውን በፈለጉ ጊዜ ከጎናቸው ይቆማል። ነገር ግን፤ የወላጆቹን መብት የነፈገናልተቀበለ፣ በእርግጥም ስብዕናው ከምክንታዊነት ተላቋል ማለት ነው፤ ስሜታዊነት የተሞላበትን የእንስሳት ጉዞ ይጀምራል።
    3. 3.ድህነትን ፈርታችሁ ልጆቻችሁን አትግደሉ፡- ኢስላም የወላጆችን መብት ብቻ በማፅደቅ አልተገደበም፤ ልጆችም መብት እንዳላቸው ይናገራል። የዚህች ዓለም ብርሀን በሚገባ ይልፋል። ጨቅላ ህፃናትም ሆኑ ቤታቸውን የእናታቸውን ማህፀንደረጉት ህፃናት መብት አላቸው። በማንኛውም ምክንት እነዚህ ህፃናት መገድል የለባቸውም የፈለገ ድህነትን ቢፈራም።። የአላህን ለጋሽነትረጋገጠ አንድ ሰው ይህን የሚፈፅምበት ምክንት አይኖረውም፤ ከርሱ ዘንድ የሚመጣ አንዳችም ሲሳይ ባለመኖሩ ይህን ለመፈፀም አይደገፍም። ህፃናት እንክብባቤ ይሻሉና ምርጥ ምርጡን ለሕፃናት መሥጠትሻል።
      1. 4.በግልፅ ሆነ በድብቅ ከሚሰሩ አስነዋሪ ተግባራት መታቀብ ፡- አስነዋሪ ተግባራት በሙሉ ቀልብንቆሽሻሉ ፤ አእምሮንጠላሻሉ። ከምክንታዊነትና ማስተንተን ጎዳናስወጣሉ። በግልፅ የሚፈፀሙ መጥፎ ተግባራት (ስርቆት፤ ውሸት፤ ነፍስ ማጥፋት፤ ዝሙት በድብቅም ሊሆን ይችላል)፤ ኢ-ፍትሀዊነት፤ ለማህበረሰቡም ጠንቅ ናቸው። ለሌሎችም የሚተላለፉ ናቸው። በድብቅ የሚፈፀሙ ተግባራት ንፍቅና (hypocricy)፤ ኢ-አማኒነት (faith lesensee)፤ ጥላቻና ጥርጣሬ ማብዛት አዕምሮንስጨንቃሉ። በፀዳ አድማስ ላይ ከማስተዋል ወደ ተጨናነቀ ዓለም አሳቤስገባሉ። ብርሀንደበዛዘሉ። ስለዚህ ማስተንተን የሚጠለሹ ሁሉም ዓይነት ሀጢት በኢስላም ይወገዛሉ።
      2. 5.ፍትሃዊ በሆነ ፍርድ በፍርድ ቤት ካልሆነ በስተቀር አንዲትም ነፍስ አንዳታልፍ (አትገደል)፡- ኢስላም ለሰው ልጅ ነፍስ ትልቅ ሥፍራን ሰጥቷል። አንዲትን ነፍስለፍትህጠፋ የሰው ልጅ ሁሉ እንዳጠፋ እንደሚቆጠርምስተምራል። በፍትህ ስንል፤ ኢስላም ከደነገጋቸው ለማህበረሰቡ ሲባል ከሚፈፀሙ በኢስላም ማዕቀፍ ሥር ካሉት ለማለት ነው። የሰው ልጅ የሌላን ሰው ነፍስ ማጥፋት የሚጀምረው አዕምሮው ማስተዋልና አርቆ ማሰብን ሲጣ ነው። በጥላቻና በንዴት የተሞላ መጥፎ አስተሳሰብ ወደዚህ ጎዳና ይመራል። በአንድ ሰው ላይ ፍትህ ማጓደል ብዙ ንፁሃንን ይጎዳል፤ ህይወታቸውንዛባል፤ በፍርሀትና በጭንቀት እንዲኖሩደርጋል።
    4. II.ታዘዛችሁ፤ ታስታውሱ ዘንድ
      1. 6.የወላጅ አጥ ህፃናትን ንብረት ጠበቅ፤ ተንከብከባቸውም፡- የሰው ልጅ ሁሌም የሚመለከተው፣ የሚከብረውና የሚውቀው የበላዩንና የጉልበተኛውን መብት ነው። አቅመ-ደካማውን ግን ማንም አስታውሰውም። ኢስላም ግን ይህን ተቃውሟል፤ የነዚህን ደካሞች መብት እንድናስታውስና እንድንጠብቅም አዟል።
      2. 7.ሚዛን አታጉድል ፤ በፍትህ ተገበይ ፤ በፍትህ ስራ፡- ገንዘብ አዕምሮንስታል፤ በገንዘብ መኖር ሲጀምር ፍትህና ሚዛናዊነት ሲረሳ አኼራ (የፍርድ ቀን) ይረሳል። ስለዚህም፤ ይህንን ፍትህና ታማኝነት በዚህም ዓለም መዘንጋት እንደሌለበትስተምራል።
      3. 8.እውነትን ብቻ ተናገሩ ፍትሐዊም ሁኑ፡- ፍትህ ከባድ ናት። ለምናውቃቸውና ለምንቀርባቸው ሲሆን ደግሞ በፍትህ መወሰን እጅግስቸግራል፤ እውነተኛ ፍርድ ይረሳል። አላህም ታዲበፍትህስታውሰናል።
      4. 9.ቃላችሁን ጠብቁ፡- ቃልኪዳንለው ስፍራ ትልቅ ነው። ቃል የሚጋቡትም፣ አደራ የሚሰጣጡበትም ሰዎች በአብዛኛው የሚተዋቀወቁና የሚዋደዱ ናቸው። ሆኖም፤ ግን በችግር ወቅት አደራችንን እንዘነጋለን። ቃላችንን እናጥፋለን። ይህ ግን መሆንለበትም፤ የትም ብንሆን ቃላችንን ልንጠብቅ፤ አደራችንን ልናስታውስ ይገባል።
    5. III.ፈጣሪችሁን እንድታውቁ፤ እንድትፈሩትም ታዘዛችሁ
      1. 10.ቀጥተኛውን፤ የፈጣሪህን መንገድ ተከትል፡- የስኬትና የደስታ መዳረሻ ፈጣሪን ማወቅ ነው። ፈጣሪውንወቀ ትዕዛዙን ይፈፀማል። ከመጥፎም ይወገዳል። ብርሃንን እንጂ ጨለማን፣ ውዴታን እንጂ ጥላቻን፣ ደስታን እንጂ ሀዘንን፣ ታማኝነት እንጂ ክህደትን፣ የፈጣሪውን ፍራቻ እንጂ አመፀኛነትን ፈፅሞ አይላበስም። በእርግጥ ሌሎች አስተሳሰቦችና መንገዶች ስህተቶች፣ ክህደትንና ውሸት ብቻ ናቸው። ኢስላም ብቻ ወደ ፈጣ ጎዳና ይመራል።   copy from http://www.ethiomuslims.net/index.php?option=com_content&view=section&layout=blog&id=1&Itemid=3

Saturday, January 21, 2012

አቢ አብዱረህማን ዐብደላህ ኢብን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል ነብዩን (ሶ.ዐ.ወ)
የትኛው ሰራ ነው ከኣላህ ዘንድ ይበልጥ በላጭ (ተወዳጁ) በማለት ጠየኳቸው።
**ሶላትን በወቅቱ መስገድ** አሉኝ

ከዚያስ ቀጥሎ? አልኳቸው ።
**ለወላጆችን በጐ መዋል** አሉኝ።

ከዚያስ ቀጥሎ? አልኳቸው ።
**በአላህ መንገድ መታገል** አሉኝ
(ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮች

• ከሻሀዳ (ተውሂድ) በኋላ አላህ በባሮቹ ላይ ያለው “ሐቅ” ሶላት ነው።
• ሰወች ከሰወች ላይ ካሏቸው መብቶች ሁሉ በላጩ የወላጆች መብት ነው
• ከመስዋዕትነቶች ሁሉ የላቀው መስዋዕትነት ደግሞ”ጂሀድ “ ነው
ምክንያቱም “ጂሀድ “ የአላህንም ሆነ የሰዎችን መብት የማስጠበቂያ መንገድ ነውና።

Sunday, January 15, 2012

. ነብዩ መሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ መናገራቸውን ኡስማን (ረ.ዐ) ዘገባ አስተላልፈዋል
** ከጀነት ደጃፍ ቆምኩ፤ (ጀነት) ከገቡት ውስጥ አብዛኞቹ ድሆች (ሆነው ኣገኝኋቸው)፤
ባለፀጋዎችና የማህበራዊ ክብር ባለቤቶች ደግሞ እንዳይገቡ ታግደው (አየኋቸው)፤

ይእሳት ሰዎች ደግሞ ወደ እሳት እንዲወሰዱ ትዕዛዝ ተላለፈ፤ ከእሳት ደጃፈ ላይ ቆምኩ፤
(እሳት )ከገቡት ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች ሆነው(አገኘኋቸው) ።** 
(ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮች
• የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሩቅ ሚስጥር (ገይብ) ስለሆኑ ነገሮች ስለ ጀነትና እሳት ሰዎች ሁኔታ መናገራቸውን ።
• በቂያማ ቀን የጀነት ሰዎች ድሆችና የመልካም ሥራ ማለቤቶች ናቸው
• የቂያማ ዕለት ከመልካም ሥራ ውጭ ገንዘብም ሆነ ልጅ ጠቀሜታ የለውም
• ከሐዲሱ ላይ “ሴቶቹ” በሚል የተጠቀሰው የሚያመለክተው አላህን የሚወነጅሉትን 
የአላህን “ሐቅ” በትክክል የማያደርሱትን መልካም ባህሪያትን ትተው ርካሽ ተግባራት ላይ የተሰማሩትን ብቻ ነው።

የትዳር ህይወትን ደስተኛ ሊያደርጎ የሚችሉ ጠቅለል ያሉ 10 አንኳር ነጥቦች



1. ከትዳር አጋርህ እውቅና ውጭ ምንም አይነት ተግባር አትፈፅም

    ይህን ማድረግ ከቻልን በትዳር አጋራችን ዘንድ ከበሬታንና ፍቅርን እናገኛለን። 
ምክንያቱም በመመካከርና በውይይት የሚያምኑ ሰዎች ለሰዎች ታይታ ሳይሆን ለህሊናቸው የሚኖሩ በመሆናቸው ሰውም ለነርሱ የሚኖረው እይታ መልካም ነው። ሰለዚህ ሰው ዘንድ ተወዳጅ ይሆናሉ።

2. ይቅር ባይ ሁኑ

    ትዳር በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች አማካኝነት የሚፈጠር የጥምረት ህይወት እንደመሆኑ መጠን ሁለት የተለያዩ አመለካከቶች፧አሰተሳሰቦችና እምነቶች መኖራቸው የግድ ነው።
የነዚህ ነገሮች መለያየት ደግሞ በእለት ተዕለት ግንኙነታችሁ ላይ አለመግባባትና ልዩነት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። 
እነዚህ ልዩነቶችም ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ።
ታዲያ እነዚህን ግጭቶች ማርገብ ተገቢ ነው። ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው ይቅርታ ጠያቂና ይቅር ባይ ሲኖር ብቻ ነው

3 በመማማር እንጂ በመወነጃጀል አትመኑ

    ሰህተትን በመተራረም እንጂ በመወነጃጀል “አንተ ነህ” “አንቺ ነሽ” በመባባል ለውጥ ሊመጣ 
እነደማይችል ሊገባን ይገባል። የሰመረ ትዳር ባለቤት የሆኑ ሰዎችም በአብዛኛው ይህንን ዓይነት ባህሪ እንመለከትባቸዋለን።

4 ፍቅርን ሰተህ ተቀበል

    የሰመረትዳር ማለት በፍቅርና በመተሳሰብ የተሞላ ግንኙነት ማለት ነው።ይህ ግንኙነት ደግሞ
ባማረ መልኩ ሊመሰረት የሚችለው ሌላኛው የትዳር አጋር እስኪያስብልንና ፍቅር እስኪሰጠን በመጠበቅ ሳይሆን መጀመሪያ እኛ ፍቅርንና እክብካቤን በመስጠት ነው። 
ሃሳባችንንና ፍላጐታችንን አውጥተን በግልጽ መናገርም ሌላኛው የሰመረ ትዳር እንዲኖርን የሚያደርግ ግብአት ነው።

5 ልዩነትን አቻችሎ መጔዝ

    የአሰተሳሰብ ችግርና ድክመቶችን ለመፍታት መሞከር አሰፈላጊ ቢሆንም የትዳር አጋራችን እኛን እንዲመስል መፈለግ ግን ፈጽሞ ተገቢ ኣይደለም ።
ሰለዚህ ማለትዳሮች ልዩነቶችን ተገንዝበው እና አቻችለው ለመሄድ በመሞከር ትዳራችውን የሰመር እና ውጤታማ ማድረግ ይችላል።



6 ይለኛል ወይም ትለኛለች የሚልን ፍርሃት አሰወግድ

    የሰመር ትዳር መገንባት የሚቻለው በማንኛውም ጉዳይ ላይ ግልፀ የሆነ ውይይት በማድረግና ስህተትን ለመቀበል ዝግጁ በመሆን ነው።
ሰለዚህ መሰረት በሌለው ነገር ላይ ይለኛል ትለኛለች እያልን የምንሰጋ ከሆነ ተዳራችን አደጋ ላይ ይወድቃል።
ይህን አይነት ሃሳብ ከማሰብ ይልቅ ሰለትዳር አጋራችን መልካም መልካሙን ነገር ማሰብና ገና በጥርጣሬ ግንኙነትን ካማሻከር መቆጠብ ያስፈልጋል።

7 ትዳር ለብልሹ ባህሪ መሸሸጊያ ኣድርጋችሁ አትውሰዱት

    እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ብዙውን ጊዜ ውጤታማ ትዳርን አያስከትልም።
ለምን ቢባል ብልሹ ባህሪ (ሱስኝነት) ማለት በመጀመሪያ ደርጃ እራስን አለመውደድ፡ማንነታችንን አለማፍቀርና ለራስ አለማሰብ ነው።
ለራስ የማያስብ ደግሞ ለትዳር አጋሩ ያስባል ባሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።
ሰለዚህ ትዳር ውሰጥ ከተገባን በኋላ ሳይሆን ከመገባቱ በፊት እንድህ አይነቱን ብልሹ ባህሪና መጥፎ አመለካከት ለማስወገድ መጣር አስፈላጊ ነው፤ 

8 የሰመር ትዳር በአንዴ አትጠብቅ

    አዳዲስ ባለትዳሮች ገና ወደ ትዳር እንደገቡ በመፅሐፍና በሌሎች የልብ ወለድ ቀመስ ታሪኮች ላይ የሚመለከቱትን አይነት ትዳር በአንድ ጊዜ እንዲመጣ ይጠብቃሉ።
ይሁን እንጂ ይህ አይነት ኣስተሳሰብ በተወሰነ መልኩ ሰህተት ነው። የሰመረ ትዳር ብዙ ጊዜ ሊፈጅ የሚችል ትልቅ የህብረተሰብ መሰረት ነው። 
ይህ የትዳር ክብርነትና ታላቅ የህይወት ክፍል ደግሞ የሰመር እንዲሆን ለማድረግ ሁኔታው የሚወሰነው እንደ ማለትዳሮቹ ቅርርቦሽ መደጋገፍና ግልፅነት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
ስለዚህ በኣንድ ጊዜ የሰመርና የተስተካካለ የትዳር ህይወትን አትጠብቁ።

9 የትዳር አጋርህን ፍላጎት ቀድመህ ለመረዳት ሞክር

    ባለትዳሮች ለትዳር አጋራቸው ሰሜትና ፍላጎታቸውን በመግለጽ ተግባብተውና ተስማምተው ለመኖር መጣር ሲኖርባቸው። 
ይህ ባልሆነበት ወቅት ደግሞ የትዳር አጋራቸውን ሰሜት ለመረዳት የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው። 


10 የሰመር ትዳር የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት እንደሆነ አስቡ

    በርካታ ባለ ትዳሮች ትዳር የፍቅር ውጤት መሆኑንና ፍቅር ደግሞ አላቂ ነገር እንደሆነ ኣድርገው ይወስዱታል።
ይሁን እንጂ ለኛና በኛ አስተሳሰብ እንጂ ፍቅር አያልቅም። ይህን የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ማድረግ ያለብንን በማድረግ ፍቅርን መገንባት እንችላለን።
ትዳር የሰመረ እንዲሆን መሰረት የሚጥለው ባለትዳሮች በችግርና በደስታ ወቅት የሚኖራቸው ምላሽ እንደሆነ ማለሞያዋ ታሰረዳለች።
ስለዚህ የሰመረና ዘላቂ የሆነ ትዳር እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ ትዳራችሁ በአጭሩ በፍቺ እንዳይደመደም የምትሹ ከሆነ ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በአግባቡ በመፈጸም ለዘላቂና ለሰመረ ትዳር አሰፈላጊውን እንድታደርጉ እንመክራለን